የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት የዛሬ መግለጫ ዋና ጉዳዮች።

173

–መንግሥት እውነቱን የሚያጣሩ ዓለም ዓቀፍ ገለልተኛ ተቋማት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲሰሩ እየሠራ ነው።

–የሽብር ቡድኑ ወርሯቸው በነበሩ የአማራና አፋር ክልሎች ጅምላ ጭፍጨፋን ጨምሮ የሰብዓዊ መብቶች መጣሱን ተከትሎ ዓለም ዓቀፉ ማኅበረሰብ እውነታውን እንዲረዳ መንግሥት እየሠራ ነው። ብለዋል፡፡

–የሽብር ቡድኖችን ተጠያቂ ለማድረግም ይሠራል፡፡

–ከዚሕ ቀደምም የሽብር ቡድኑ ወርሯቸው በነበሩ የአማራና የአፋር ክልሎች ጅምላ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ሂውማን ራይትስወች አስታውቋል፡፡

–አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች ያደረሳቸውን ጥፋቶች በመለየት ክስ የመመስረት ሥራን የሚከውን ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሠራ ነው፡፡

–ግብረ ኀይሉ በተመሳሳይ የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ይሠራል፤ ኢትዮጵያ የምትመራባቸውን ዓለም ዓቀፍ ሕግጋት በመከተል ተጠያቂ ለማድረግ ይሠራል፡፡

Previous article“እውነተኛ ዴሞክራሲ የሚሰፍነው በሀገራት ላይ ጣልቃ ገብነት ሲቆምና ህዝቡ የራሱ ዴሞክራሲ ባለቤት ሲሆን ነው”
Next articleበጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የበቃ ዘመቻን በመቀላቀል ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙ አስታወቁ