
ሕዳር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውየር ሀገራቸው የኢትዮጵያ የልማት አጋር መሆኗን ገልጸዋል። የወከሉት መንግሥት ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ እንደሚደግፍ አስታውቀዋል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውየርን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።
በውይይቱ ላይ ዶክተር ፍፁም ኢትዮጵያ እየተገበረች በምትገኘው የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ገለጻ አድርገዋል።
ኢትዮጵያ ከልማት ትብብር የምታገኘውን ድጋፍ በተመለከተ አንስተዋል። ድጋፉ ቀላል የማይባል እና የማይናቅ መሆኑን ጠቅሰዋል።
አምባሳደር ስቴፋን አውየር የጀርመን መንግሥት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አመራርን እንደሚደግፍ ገልጸዋል። ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ተባብሮ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆኑንም አመላክተዋል።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍፁም አሰፋ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውየር መካከል በተደረገው ውይይት በቀጣይ ኢትዮጵያ እና ጀርመን በተለያዩ ዘርፎች በኢንቨስትመንትና ልማት ፕሮግራሞች ትብብራቸውን ለማጠናከር ተስማምተዋል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation