በኮምቦልቻ፣ በአንጾኪያ ገምዛ እና በጋሸና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ።

178
አዲስ አበባ፡ ሕዳር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ በሰጡት መግለጫም በኮምቦልቻ፣ በአንጾኪያ ገምዛ እና በጋሸና የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን አስታወቀዋል። ቡድኑ ወሯቸው በነበሩ አካባቢዎች ሰፊ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት ማድረሱንም ተናግረዋል።
የሰብዓዊ መብት ቀን ነገ ሲዘከርም እነዚህንና ማይካድራን፣ ጭናን፣ ቆቦን፣ አጋምሳን፣ ጋሊኮማናን እና ሌሎች የንጹሃን እልቂቶችን በማሰብ ይዉላል ነው ያሉት።
አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡደን ለመደምሰስ እየተካሄደ በሚገኘው ዘመቻ ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት አስደናቂ ጥምረት የታየበት ነዉ ብለዋል፡፡ በዚህም አሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለማጥፋት በተደረገው ትግል ከፍተኛ ድል መገኘቱን ሚኒስትሩ ዶክተር ለገሰ ቱሉ ገልጸዋል።
በአሸባሪው ቡድን የወደሙትን መሠረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት መንግስት እየሰራ መሆኑንም ዶክተር ለገሰ ገልጸዋል።
በኦሮምያ ክልል ኦነግ ሸኔን ለማጥፋት በተደረገዉ ዘመቻም ትልልቅ ድሎች ተገኝተዋል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ – ከአዲስ አበባ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleደጀንነት በተግባር…
Next articleጀርመን ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ እንደምትደግፍ አስታወቀች።