“አፍሪካ በተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ አለማግኘቷ አሳዛኝ ነው” የአፍሪካ መሪዎች

329
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ እና የሴኔጋሉ አቻቸው ማኪ ሳል አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ቋሚ ውክልና አለማግኘቷ ፍትሐዊ እንዳልሆነ አስታውቀዋል፡፡
ራማፎዛ በዳካር በተካሄደው የአፍሪካ የሰላም እና ጸጥታ ጉባዔ ላይ አፍሪካ በጸጥታው ምክር ቤት በተገቢው መንገድ እንድትወከል መደረግ አለበት ብለዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ትናንት ማስታወቃቸው ይታወሳል።
አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እና ተሰሚነት እንዲኖራት ሌሎች አፍሪካውያን መሪዎች እያደረጉት ያለውን ንቅናቄ መቀላቀላቸውንም ገልጸዋል።
የአህጉሪቱ ተወካይ በሌለበት አህጉሪቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች መከናወናቸው ሊቀጥል አይገባም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአንቶኒዮ ጉቴሬስና ከሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።
Next articleደጀንነት በተግባር…