‟ጠላትን አጥፍተን ኢትዮጵያዊነታችንን እናሳያለን” የወሎ ግንባር የክተት ዘማቾች

273
ሕዳር 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የወሎ ግንባር የክተት ዘማቾች የሽብር ቡድኑን ሥር ለመንቀል በጀግንነት እየተፋለሙ ነው። ጀግኖች ማንነት ተደፈረ ሀገር ተወረረ ሲባል ነው ወደ ግንባር በመዝመት ጠላትን እየደመሰሱ የሚገኙት።
በወሎ የገባውን የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን እንደ ቋያ እሳት እየለበለቡት ነው። ጀግኖቹ ጠላትን ድምጥማጡን ሳያጠፉና ሥሩን ሳይነቅሉ እንደማይመለሱም ገልፀዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን የሰላምና ደኅንነት መምሪያ ምክትል ኀላፊ አታላይ ይልቃል የተቀናጀው የወገን ጦር በወሎ ግንባር በገባበት አውደ ውጊያ በጠላት ላይ የበላይነት በመውሰድ ጠላትን እየደመሰሰው መሆኑን አስታውቀዋል። ወደ ፊት እንጂ ወደ ኋላ የሚል ኀይል እንደሌለም ተናግረዋል። ጠላት ቆሞ ሊዋጋቸው በማይችልበት ቁመና ላይ መድረሱንም አስረድተዋል። የወገን ጦር ጠላትን ድምጥማጡን እያጠፋ ወደፊት እየገሰገሰ መሆኑን ነው ያብራሩት።
የወገን ጦር አባል ታያቸው ጥሩነህ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኑ ተላላኪዎችንም ሲደመስሱ እንደቆዩ ገልጸዋል። ‟ጠላትን አጥፍተን የአማራን ማንነት ለማሳየት ነው የመጣነው፤ ዓላማችን ከወገን ጦር ጋር በመቀናጀት ጠላትን ድባቅ መምታት ነውም“ ብለዋል። ጠላት ምን እንደምናደርገው እና እንዴት እንደምንደመስሰው ያውቀናል ያሉት አባሉ የአማራን ማንነትና የኢትዮጵያን አንድነት እናሳያቸዋለን ነው ያሉት። መነሻው የኢትዮጵያ አንድነት ነው፣ ታሪክ ተሠርቷል፣ ወደፊትም ታሪክ ይሠራል ብለዋል።
የወገን ጦር ጥምረት ጠላትን እያርበደበደው መሆኑን እና ለሀገር መሠረት የሆነ ጀግና ሠራዊት መኖሩንም አስታውቀዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ!!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየወገን ጦር የድል ግስጋሴውን እንዲቀጥል ሕዝቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት አቤት ኃላፊ ኮሎኔል ባምላኩ ዓባይ ገለጹ።
Next articleከ200 ሺህ በላይ ሕዝብ የሚገለገልበት ሆስፒታል ሙሉ በሙሉ ወድሟል።