
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “የ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ሕዝብ መኖሪያ የሆነችው አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ ሊኖራት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት፣ አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እና ተሰሚነት እንዲኖራት ሌሎች አፍሪካውያን መሪዎች እያደረጉት ያለውን ንቅናቄ መቀላቀላቸውን አሳውቀዋል።
የአህጉሪቱ ተወካይ በሌለበት አህጉሪቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች እና ውሳኔዎች መከናወናቸው ሊቀጥል አይገባም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመልእክታቸው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation