
ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በ“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” እየተመዘገበ ያለው ድል በኢትዮጵያ ላይ የሚነሱ ጠላቶች ኹሉ ተሸንፈውና ተዋርደው የሚመለሱ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ሲሉ በግንባር የተገኙ አርቲስቶች ተናገሩ።
የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የፈጸመውን ወረራ ለመመከት እየተደረገ ባለው የህልውና ዘመቻ የመላ የኢትዮጵያዊያን ተሳትፎና አንድነት ይበልጥ ተጠናክሮ የታየበት፣ በጋራ ክንድ ጠላት እየተመታ ያለበት አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል።
አርቲስት ተሾመ አየለ (ባላገሩ) እና አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን “ኢትዮጵያዊያን አንድነታችን ይበልጥ እየተጠናከረ በመምጣቱ ሊበትነንና በህልውናችን መጥቶ ሊበግረን የሚችል ጠላት የለም” ብለዋል።
“ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በሚል እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያን ህልውና የማስጠበቅ ዘመቻ በኢትዮጵያ ላይ የሚነሱ ጠላቶች ኹሉ በቁርጥ ቀን ልጆቿ ተዋርደውና ተሸንፈው የሚመለሱ መሆኑን ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል።
“ኢትዮጵያን እናፈርሳለን” በማለት የተነሱት አሸባሪና ባንዳዎች እንዲሁም የውጭ ጠላቶች ሳይሳካላቸው ሐፍረት እየተከናነቡ መሆኑን አርቲስት ተሾመ አየለ (ባላገሩ) ተናግሯል።
በኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ተጋድሎ እየተገኘ ያለው ድል ኢትዮጵያን ዳግም ከፍ ያደረገ ልዩ የታሪክ አጋጣሚ መሆኑንም ጠቅሷል።
ለኢትዮጵያ ህልውና እየተዋደቀ የሚገኘውን የወገን ጦር መደገፍ እንደሚገባ መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
በጦርነቱ የተጎዳውን ኢኮኖሚ መልሶ ለማነቃቃት በሰዓት ሳንገደብ የምንሠራበት ሌላው የህልውናችን ጉዳይ ነው ሲልም ተናግሯል።
አርቲስት ሚካኤል ሚሊዮን በበኩሉ የወገን ጦር እያደረገ ያለው ተጋድሎ ለሀገሩ ያለውን ጽኑ ፍቅር የሚያሳይ በመሆኑ ኹላችንም አብረን ልንሰለፍ ይገባል ብሏል።
የኢትዮጵያ ጥምር ኃይል ለሀገሩ ህልውና ሲል በጀግንነት እየተፋለመ ጠላትን በየግንባሩ ድል እያደረገ ያለበት መንገድ የሚደነቅ መሆኑንም ጠቅሷል።
ኢትዮጵያን በወረራ ለማንበርከክ የሞከሩት የጥፋት ኃይሎች ኹሌም የማይሳካላቸው መሆኑን በጋራ ክንዳችን አረጋግጠናል ነው ያለው።
ኢትዮጵያ የተደቀነባትን የህልውና አደጋ በመመከት ያስመዘገበችው ድል ለመላ አፍሪካዊያን ሌላኛው የአሸናፊነት ተምሳሌት ነው ሲልም ተናግሯል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation