
ባሕርዳር፡ ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
-የውጭ ጣልቃ ገብነትን ለማስቆም ኢትዮጵያ የሄደችበት ርቀት እና የተገኘ ውጤት መኖሩ፡፡
-ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሽብር ቡድኑን ለመደምሰስ የሚደረገው ርብርብ፣ በጦርነቱ በደረሰው ውድመት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ በተለያዩ አካባቢዎች ሰልፍ መካሄዱ እና ገቢ መሰብሰብ መቻሉ፡፡
-የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ባስተላለፉት ጥሪ መሠረት 1 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ሀገር ቤት መጥተው ትግሉን ለመቀላቀል እና የተቀዛቀዘውን ቱሪዝም ለመደገፍ እንቅስቃሴ መጀመሩ እና አበረታች ውጤት መመዝገቡ፡፡
-ዘመቻውን ለመደገፍ ለሚመጡ አካላት የአየር መንገድን ጨምሮ ሌሎች አገልግሎት ሠጪ ተቋማት የዋጋ ቅናሽ እንደሚያደርጉ፡፡
-የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በአፍሪካ የሰላም እና የጸጥታ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የዓለም ሀገራት በአፍሪካ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት አላስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው እንዲያቆሙ ማስረዳታቸው
-በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለው አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነት እንዲቆም እና የዓለም የሰላም አስከባሪ ኀይላት መደበኛ ያልሆነ ወታደራቸውን በየቦታው ማስፈራቸውን እንዲያቆሙ መጠየቃቸው፡፡
-ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልል ከባድ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመት በማድረስ ዘመኑን የማይመጥን የሰብዓዊ መብት ጥሠት ፈጽሟል፤ ነገር ግን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አካላት ችግሩን በጸጥታ ከማለፍ ባሻገር ችግሩን ወደ ኢትዮጵያ ከማዞር እንዲቆጠቡ መንግሥት አስፈላጊውን ሥራ እየሠራ መሆኑ፡፡
-መንግሥት በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች እርዳታ እያደረሰ መሆኑ፣ የተለያዩ እርዳታዎች እንዲገቡ መፍቀዱ እና የአየር በረራዎች መፈቀዳቸው በዋናነት የተጠቀሱ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ