ሕብረብሔራዊነት ለኢትዮጵያ አንድነት ፅኑ መሰረት እንዳለው ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።

95
ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሕብረ ብሔራዊነት ለኢትዮጵያ አንድነት ፅኑ መሰረት እንዳለው ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ገልጸዋል።
16ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በድሬዳዋ ከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡
ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስን ጨምሮ ሌሎች የፌደራልና የክልል መንግሥታት የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን በመድረኩ ተሳታፊ ሆነዋል።
ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ባደረጉት ንግግርም ሕብረ ብሔራዊነት ለኢትዮጵያ አንድነት ፅኑ መሰረት እንዳለው ገልጸው፤ ኢትዮጵያ የተለያየ ቋንቋ፣ ሃይማኖትና ባህል ተቻችሎና ተፈቃቅዶ መኖር እንደሚቻል የሚታይባት ሀገር መሆኗን አንስተዋል፡፡
ወቅቱ ሀገር ፈተና ውስጥ የወደቀችበት የሀገር ሃብትና ንብረት የወደመበትና መፈናቀል የሚስተናገድበት ቢሆንም የማይነጋ ሌሊት እንደሌለ ኹሉ ከጦርነት በኋላ ሰላም እንደሚኖር ገልጸዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ወገኖች መድረስ እንደሚገባ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የፈረሱ መሠረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት የኹሉም ርብርብ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
ፕሬዚዳንቷ ለሀገር ህልውና በግንባር እየተዋደቀ ላለው ጀግናው የወገን ጦር የዲፕሎማሲ ሥራ በመሥራት ላይ ያሉ ዳያስፖራዎችን አመስግነዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር በበኩላቸው “ይህንን ቀን ስናከብር አንድነታችንን ጠብቀን በጋራ ጥቅማችን ላይ በጋራ ለመሥራት ቃል በመግባት ሊሆን ይገባል” ብለዋል፡፡
“ብዝሃነታችን ብርታታችንን አልቀነሰውም ውበታችንን ያደምቀዋል እንጂ አያደበዝዘውም” ነው ያሉት፡፡
“አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ላይ ቀይ መስመር ያለፈ ድርጊት ፈፅሟል” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“አሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ቡድን “ለማጥፋት በተደረገዉ ዘመቻ የተገኘዉ ድል የኢትዮጵያዉያን የሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ያሳየ ነዉ” የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት
Next article“በድል የታጀበው የመጀመሪያው ምእራፍ”