“አሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ቡድን “ለማጥፋት በተደረገዉ ዘመቻ የተገኘዉ ድል የኢትዮጵያዉያን የሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ያሳየ ነዉ” የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት

169
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በመግለጫቸውም “አሸባሪዉን የትግራይ ወራሪ ቡድን “ለማጥፋት በተደረገዉ ዘመቻ የተገኘዉ ድል የኢትዮጵያዉያን የሕብረ ብሔራዊ አንድነትን ያሳየ ነዉ” ብለዋል፡፡
ድሉ አሁንም ተጠናክሮ ቀጥሏል በዚህ ድል ከማንኛውም ጊዜ በተለየ ሁኔታ የኢትዮጵያውያን አንድነትና ጥንካሬ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ለድሉ መገኘት የወገን ጦር ቅንጅትና ጥምረት ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል፡፡
ያለፈው ሳምንት በዲፕሎማሲያዊ ሥራዎች ውጤት የተገኘበት እንደነበርም አንስተዋል፡፡ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የተጀመረው የበቃ ወይም “No More ንቅናቄ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡
አንድ ሚሊየን ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ወደ ኢትዮጵያ ኢንዲገቡ ለማድረግ መንግሥትና ባለድርሻ አካላት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወኑ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከትኬት ዋጋ 30 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ጠቅሰዋል፡፡ የቱሪስት አግልግሎት ሰጭ ተቋማት ከአገልግሎታቸው ተመሳሳይ የዋጋ ቅናሽ እንደሚያደርጉም ይጠበቃል ነው ያሉት፡፡
ለተግባሩ ዉጤታማነትም ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል ብለዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል የኢትዮጵያን ገጽታ እንዲገቡና ቱሪዝሙን እንዲያነቃቁ ጥሪ መቅረቡን ገልጸዋል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
Previous article“ኢትዮጵያ የከበቧትን ጠላቶቿን እያሸነፈች ያለችው ኢትዮጵያዊነት በተባለው ከኢትዮጵያ ብቻ ሊመነጭ በሚችለው ልዩ ኃይል ነው” ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት
Next articleሕብረብሔራዊነት ለኢትዮጵያ አንድነት ፅኑ መሰረት እንዳለው ፕሬዚዳንት ሳኅለወርቅ ዘውዴ ገለጹ።