በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሠራተኞች ገንዘብ በማዋጣት ለወገን ጦር ስንቅ እያዘጋጁ ነው፡፡

183
ጎንደር፡ ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምሕራን እና ሰራተኞች ከዚህ ቀደም የወር ደመወዛቸውን ለሕልውና ዘመቻው የለገሱ ቢሆንም የተጀመረውን ዘመቻ በድል ለማጠናቀቅ አሁንም የደጀንነት ሚናን ማጠናከር ተገቢ በመሆኑ መምሕራን እና ሰራተኞች ገንዘብ አዋጥተው ተጨማሪ የስንቅ ዝግጅት እና ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረጉ ነው፡፡
በኮሌጁ የስንቅ ዝግጅት ሥራ ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው አምሳሉ ፈለቀ (ፕሮፌሰር ) እና ወይዘሮ ወይንሸት ገድሉ ለሕዝብ ሕልውና በግንባር ጀብድ እየፈጸሙ ላሉ የፀጥታ ኀይሎች ቀጣይነት ያለው የድጋፍ ሥራ እየሠሩ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የሕክምናና ጤና ሳንስ ኮሌጅ ስፔሻላዝድ ሆስፒታል ዋና አካዳሚክ ዳይሬክተር አስማማው አጥናፉ (ዶክተር) በግቢው የሎጅስቲክ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሞ ሰፊ ሥራ እየተሠራ መሆኑን ነግረውናል፡፡ በተለያየ መንገድ ከተሰበሰበው 2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ውስጥ ወጭ በማድረግ 50 ኩንታል የተምር ስንቅ እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ አሸናፊ ታዘበው (ዶክተር) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ያወደማቸውን የጤና ተቋማት ቁሳዊ እና መዋቅራዊ ጉዳት በማጥናት ኅብረተሰቡ ከደረሰበት ከፍተኛ የሕክምና እጦት ችግር እንዲላቀቅ አቅም በፈቀደ መልኩ ለማገዝ እና የወደሙ የጤና ተቋማትን ለማስጀመር እየተሠራ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
ከጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተጨማሪ በማራኪ፣ በአጼ ቴዎድሮስና በፋሲል ግቢ የሚገኙ መምሕራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ኩኪስ እና ዳቦ ቆሎ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ሲሳተፉ ተመልክተናል፡፡
በየግቢው የስንቅ ዝግጅቱን እና ሌሎች የደጀንነት ሥራዎችን በማስተባበር ላይ የሚገኘ ሰራተኞች ለአሚኮ እንደተናገሩት የሚዘጋጀው ስንቅ ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን በማሽን እየታገዘ ነው፡፡
ዘጋቢ፡- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ-ከጎንደር
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
Previous article“የሽብር ቡድኑ ግፍ በዋግ ሕዝብ ላይ”
Next article“ኢትዮጵያ የከበቧትን ጠላቶቿን እያሸነፈች ያለችው ኢትዮጵያዊነት በተባለው ከኢትዮጵያ ብቻ ሊመነጭ በሚችለው ልዩ ኃይል ነው” ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት