
ሕዳር 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ወረራ የፈፀመው የአሸባሪው የትግራይ ቡድን በመከላከያ ሠራዊት በአማራ ልዩ ኃይል፣ በፋኖና ሚሊሻ እየተቀጠቀጠ ነው። የሽብር ቡድኑ የሚደርስበትን ከባድ ምት ሊቋቋም ባለመቻሉ በወረራ ይዟቸው የነበሩ አካባቢዎችን እየለቀቀ እየፈረጠጠ ነው።
ለአሚኮ ሀሳባቸውን የሰጡ የጀግናው የአማራ ልዩ ኃይል አባላትም ተቅለብልቦ በአማራ ክልል ወረራ የፈፀመውን የሽብር ቡድን ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመሆን እያጣደፉ እየደመሰሱት መሆናቸውንም ተናግረዋል። ሠራዊቱ የጠላትን ምሽጎች እየሰባበበረ ወደ ፊት እየገሰገሰ እንደሚገኝም ገልጸዋል።

የአማራ ልዩ ኃይል በከፍተኛ ወኔ እየገሰገሰ ጠላትን ድባቅ እየመታው መሆኑንም አስታውቀዋል። ጠላት የያዛቸውን ምሽጎች በቀላል መስዋእትነት መስበር መቻላቸውንም ተናግረዋል። ጠላት የመዋጋት አቅሙ የደከመና ከወገን ጦር ግንባር የመቆም አቅም እንደሌለውም አስታውቀዋል። ጠላትን ከአማራ ክልል ማፅዳት ብቻ ሳይሆን የወሰደውን ሁሉ በገባበት ገብተን እናስመልሳለንም ነው ያሉት።
ኢትዮጵያን ነፃ ለማውጣትና ጠላቶቿን ለማጥፋት የምንሰስተው ነገር አይኖርምም ብለዋል። ትግሉና ድሉ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። የወገን ጦር የጀግና ጀግና ነው ያሉት አባላቱ በአንድ ቀን ብቻ በርካታ ምሽጎችን መስበር እንደተቻለ ነው የተናገሩት።

ኢትዮጵያ የጀግኖች ሀገር በመሆኗ ጠላቶቿ በሚመኙላት ሳይሆን ጀግኖቿ በሚመትሩላት መንገድ ትጓዛለችም ብለዋል።
የአማራ ልዩ ኃይል አስደናቂ ድሎችን እና ጀብዱዎችን መፈፀሙን እና እየፈፀመ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል። ጠላት የሚተማመንባቸው ምሽጎችን በአጭር ጊዜ እንደሰባበሩትም ተናግረዋል። ልዩ ኃይሉ የሚገርም የውጊያ ስልትና ጀግንነትን የተላበሰ መሆኑንም ገልፀዋል። ምንም አይነት ፈተና ሳይበግራቸው ጠላትን በየገባበቱ እየገቡ በሚገባ እየቀጡት መሆናቸውንም አስታውቀዋል። የጠላት አቅም የተልፈሰፈሰ ነው ያሉት አባላቱ ጠላትን የመረጥነው ቦታ ላይ እየመታን መውጫ መግቢያ አሳጥተነዋልም ብለዋል። በየቀኑ አስከሬን እንደ ስንቅ እንደሚያስጭኑትም ተናግረዋል።
ጠላት ከሆነለት በየትኛውም ግንባር ይሁን ይጠብቀን፣ ክልላችን ደፍሯል፣ የጀግኖች ልጆች ጀግኖች ምን እንደሆን እናሳየዋለን ይጠብቀን ነው ያሉት።

ዘጋቢ :- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation