በወገን ጦር ድባቅ ተመትቶ የተበታተነውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ሕዝቡ በየቀዬው ተደራጅቶ #እንዲቀብረው የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ አቀረቡ።

203
ሕዳር 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ በወገን ጦር የተቀናጀ ምት ነፃ የወጡ አካባቢዎች በአፋጣኝ ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንዲመለሱ እየተሠራ መሆኑን የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አሰተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን ገልጸዋል።
ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ቆይታ ያደረጉት የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አብዱ ሁሴን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወርራቸው የነበሩ አካባቢዎች በወገን ጦር እየደረሰበት ባለው ከፍተኛ ምት ነፃ እየወጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዋና አስተዳዳሪው ነፃ በወጡ አካባቢዎች ማኅበረሰቡ ወደ መደበኛ ሕይወቱ በፍጥነት እንዲመለስና ሥራዎች በእቅድ እንዲመሩ መሪዎች ኀላፊነት ተሰጥቷቸው እየሠሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል። በተለቀቁ አካባቢዎች ሰላምና ፀጥታውን ለማስጠበቅ የፖሊስ አባላት በፍጥነት እንዲመለሱና መደበኛው የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲጀምር ተደርጓል ነው ያሉት።
ነፃ በወጡ አካባቢዎች መሠረተ ልማቶችን የመጠገን እና አገልግሎት እንዲጀምሩ የሚያደርግ ኮሚቴ ተቋቁሞ የቴሌኮምዩኒኬሽንና የመብራት ኃይል ባለሙያዎች ከሥር ከሥር እየተከታታሉ እየሠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።
የሁለቱ ተቋማት ባለሙያዎች ከፍተኛ ምስጋና ይገባቸዋልም ብለዋል። ሌሎች ተቋማትም ከቴሌኮምዩኒኬሽን እና ከመብራት ኃይል ትምህርት ወስደው ወደ ሥራቸው በፍጥነት እንዲገቡ ነው ዋና አስተዳዳሪው የጠየቁት።
የባንክ አገልግሎት ዘግተው የነበሩ ከተሞችም አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውንም አስታውቀዋል።
በከተሞች አካባቢ ሕዝቡ በውኃ እንዳይቸገር በተሸካርካሪ እያቀረቡ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የጤና ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት እንዳደረሰ የተናገሩት ዋና አስተዳዳሪው የክልሉ መንግሥት ያቋቋመው የጤና ቡድን ከሥር ከሥር እየተከታተለ፣ የጉዳት መጠኑን እየለየ እና በአጭር ጊዜ ሥራ እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል።
አቶ አብዱ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን በቀጥታም ኾነ በተዘዋዋሪ የደገፈ አካል በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንደሚሆንም ተናግረዋል። ጠላትን በደገፈ አካል ላይ ያለ ምንም ድርድር እየተለዬ አስፈላጊው እርምጃ ይወሰድበታልም ብለዋል።
ወረራ በተፈፀመባቸው አካባቢዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ አካባቢያቸው መመለስ የሚያስችል ኮሚቴ በአፋጣኝ እንደሚቋቋምና የተዘረፈባቸውን ንብረት ቆጥሮ እንዲያሳውቅም ይደረጋልም ነው ያሉት።
አቶ አብዱ ዓለም አቀፍ ረጂ ድርጅቶች የፖለቲካ ፍላጎታቸውን ትተው ለእውነት፣ ለሰብዓዊነት እና ለዴሞክራሲ የሚቆሙ ከኾነ በችግር ውስጥ ላለው ማኅበረሰብ የሚቻላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሕዝቡ እስካሁን በተደረጉ አውደ ውጊያዎች የሚጠበቅበትን ደጀንነት እየፈፀመ መሆኑንም ተናግረዋል። ሕዝቡ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ፣ ስለ ጠላት እንቅስቃሴ ለጸጥታ ኃይሉ መረጃ በመስጠት በኩል አኩሪ ተግባር እየፈፀመ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
ሕዝቡ ተጨማሪ ወሳኝ ኀላፊነት አለበት ያሉት ዋና አስተዳዳሪው በወገን ጦር ድባቅ ተመትቶ የተበታተነውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሕዝቡ በየቀዬው ተደራጅቶ፣ ደመኛ የሆነው ጠላት የያዘውን ንብረት ይዞ እንዳይወጣ እና ወሎ ምድር ላይ እንዲቀበር በንቃት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ተመልሶ የሀገር ስጋት በማይሆንበት ደረጃ #መቅበር እንዲቻል ሕዝቡ መማረክ የሚቻለውን እንዲማርክ እምቢ ያለውን ደግሞ እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል፡፡
አቶ አብዱ ማንንታችን እንዲከበርና ከሌሎች ሕዝቦች ጋር እንድንኖር ደመኛ የሆነው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን #መጥፋት አለበት ብለዋል። የአማራ ሕዝብ ጠላትን ባለበት በማስቀረት ኀላፊነቱን ከተወጣ ዘላቂ ሰላም እንደሚመጣም ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleበአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው፡፡
Next articleየዋግ ሚሊሻ እና ሕዝብ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በማስቀጠል የአባቶቹን ታሪክ እንዲደግም በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ክላስተር አስተባባሪ ስዩም መኮንን አሳሰቡ።