በአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ ሊካሄድ ነው፡፡

115
ሕዳር 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሜሪካ ሁሉም ግዛቶች የሚኖሩ ዳያስፖራዎች የሚሳተፉበት ሰላማዊ ሰልፍ በዋሺንግተን ዲሲ የፊታችን አርብ ይካሄዳል።
ሰልፉ የፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና በመቃወም እንደሚካሄድ ተገልጿል።
የሰላምና አንድነት ለኢትዮጵያ ማኅበር ዋሺንግተን ግብረ ኃይል አባል አቶ ከባዱ በላቸው፥ ሰልፉ በኢትዮጵያ የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 11 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድ ለኢዜአ ገልጸዋል።
ሰልፉ መነሻውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አድርጎ የአሜሪካ መንግሥት መቀመጫ ወደ ሆነው ‘ካፒቶል ሂል’ መድረሻውን እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
ሰልፈኞቹ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርገውን ያልተገባ ጫና የሚቃወሙ መልዕክቶችን እንደሚያስተላልፉም አመልክተዋል።
ሰልፈኞቹ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን እየፈጸማቸው ያሉ አሰቃቂ ድርጊቶች እና የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙኀን በኢትዮጵያ ዙሪያ የሚያሰራጯቸውን ሐሰተኛ መረጃዎችን እንደሚያወግዙም ገልጸዋል።
በአሜሪካ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በሰልፉ ላይ በህልውና ማስከበር ዘመቻው ከኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ጎን መቆማቸውን የሚገልጹበት መሆኑንም ነው አቶ ከባዱ ያስረዱት።
አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የምታደርገውን ያልተገባ ጫና እንድታቆም የሚያስገነዝብ ደብዳቤ ለአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት እንደሚሰጥም ጠቁመዋል።
ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አንስቶ እስከ ‘ካፒቶል ሂል’ በሚደረገው የአንድ ሰዓት የእግር ጉዞ ለአሜሪካ ዜጎች በኢትዮጵያ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ የተመለከቱ መረጃዎችን የያዙ በራሪ ወረቀቶች እንደሚበተኑም አመልክተዋል።
በሰልፉ ላይ በኹሉም የአሜሪካ ግዛቶች የሚኖሩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው አቶ ከባዱ ያብራሩት።
የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን በየሚኖሩባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሴናተሮችና የኮንግረስ አባላት በሰልፉ ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደቀረበላቸውም አመልክተዋል።
ዳያስፖራው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግን ጨምሮ እያከናወናቸው ባሉ የዲፕሎማሲ ሥራዎች የተወሰኑ ሴናተሮችና የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት በኢትዮጵያ ላይ እያሳዩ ያለው አቋም መሻሻል እየታየበት መሆኑንም ነው የገለጹት።
የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በተለያዩ አማራጮች የአሜሪካ መንግሥት ላይ ጫና ማድረጉን እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡ ለኢትዮጵያ በተለያዩ መስኮች እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚቀጥልም ነው የገለጹት።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“ትናንት በታላቅ አዳራሽ ነበር የሚያጌጡ፤ ዛሬ ቀን ጥሏቸው እኩይ ሰው ገፍቷቸው በአመዱ ላይ ተቀመጡ”
Next articleበወገን ጦር ድባቅ ተመትቶ የተበታተነውን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድንን ሕዝቡ በየቀዬው ተደራጅቶ #እንዲቀብረው የደቡብ ወሎ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጥሪ አቀረቡ።