“ኢትዮጵያ ፈርሳ የቀድሞው ኢትዮጵያዊ መባል ስለማልፈልግ ነው የህልውና ዘመቻውን የተቀላቀልኩት” አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ

180
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዓለም መድረክ ኢትዮጵያ በኩራት እንድትጠራ አድርጓል። ምናልባትም በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በርካቶች መሆን የሚፈልጉት አይነት የስኬት ሰው ነው አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ። የአትሌቲክስ ፈርጥ እየተባለ የሚጠራው ስመጥር ሯጩ ሻለቃ ኀይሌ፡፡
ይህ ጀግና በበርካታ ክብረወሰኖች ሀገሩን ለሜዳሊያ ሽልማት እንደበቃ ሁሉ ለሚወዳት ሀገሩ ውለታ ይሆንለት ዘንድ በርካታ ባለኮከብ ሆቴሎችንና ሪዞርቶችን በመገንባት ባለክብረወሰን የቱሪዝም ኢንዱስትሪው ጀግና መሆን የቻለ እንቁ ኢትዮጵያዊ ነው።
ሻለቃ ኀይሌ ኢትዮጵያ ፈርሳ የቀድሞው ኢትዮጵያዊ መባል ስለማልፈልግ ነው የህልውና ዘመቻውን የተቀላቀልኩት ሲል ተናግሯል። ይሔንን ውሳኔውንም ቤተሠቦቹ እንደደገፉለትም ገልጿል።
ሻለቃ ኀይሌ የኢትዮጵያን ችግር በሽምግልና ለመፍታት ብዙ የደከመ ሠው ነው። ለዚሁ ተግባር በራሡ ወጭ ቻርተር አውሮፕላን እየተከራየ ለኢትዮጵያ ሲል ወደ መቀሌ ለሽምግልና ተመላልሷል። ሞገደኛው አሸባሪው ትህነግ ግን ይህን አለም እንቁ ብሎ በልዩ አክብሮት የሚጠራውን ታላቅ ሠው ከቁብ ሊቆጥረው አልቻለም። እብሪቱ የወጠረው አሸባሪው ትህነግ የጓዳ ነውሩን አደባባይ ይዞት ሀገር ለማውደም ሲነሳ አትሌት ኀይሌ ይህንን የጥፋት ቡድን ሊታገሠው አልቻለም።
አትሌት ኀይሌ በይፋ ይህን አሸባሪ የትግራይ ቡድን ጨርቄን ማቄን ሳይል ለመፋለም መወሰኑን ይፋ አድርጎ ዘመተ። በበርካታ ግንባሮችም በመገኘት ሠራዊቱን ማነቃቃቱን እና ቀጥተኛ ድጋፍ ማድረጉን ቀጥሏል።
አትሌት ኀይሌ ይህን ሁሉ የሚያደርገው ኢትዮጵያን ከመፍረስ ለመታደግ እና ሀገር አልባ ላለመሆን ነው። በኀይሌ መዝመት ብዙዎች ተደንቀዋል። ይሔ መደነቃቸውም ምክንያታዊ እና ከኢትዮጵያ ውጭ በሚገኙ ሀገሮችም እንግዳ ነገር በመሆኑ ነው። ምክንያቱም ማንም በዓለም ክብረ ወሰን ስመጥር የሆነ ሰው የቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንቱን ከቁብ ሳይቆጥር ወደጦር ግንባር የዘመተ የዓለም ታዋቂ ሰው ባለመኖሩ ነው።
አትሌት ኀይሌ የዘመተላት ኢትዮጵያ ለሚወዷት ሁሉ ህያው ሆና ትቀጥላለች እንጅ ነበረች ልትባል አትችልም። ኢትዮጵያ የጀግኖች እናት በመሆኗ ለህልውናዋ የዘመቱላት መሪዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እንዳሉት ተስፋ መቁረጥን ራሱ ተስፋ እያስቆረጠች በልጆቿ መስዋእትነት ትቀጥላለች።
በሀብተጊዮርጊስ አበይ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ቆራጥ መሪዎቿና ልጆቿ አፍራሾቿን እያፈረሷቸው ነው” አቶ ጋሻው መርሻ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአደረጃጀት ክፍል ኀላፊ
Next articleበኩር ጋዜጣ ሕዳር 27/2014 ዓ.ም ዕትም