“ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ቆራጥ መሪዎቿና ልጆቿ አፍራሾቿን እያፈረሷቸው ነው” አቶ ጋሻው መርሻ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአደረጃጀት ክፍል ኀላፊ

233
ሕዳር 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይልን ለማጥፋት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሀብቶች፣ ምሁራን፣ አርሶ አደሮች እንዲኹም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ኹሉ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ። በትግሉ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በየግንባሩ በመዝመት፣ ለወገን ኀይል ሞራል ይሰጣሉ፣ ድጋፍ ያደርጋሉ፣ ሕዝቡን ወደ ግንባር በማዝመት የህልውና ትግሉ እንዲያፋፋም እያደረጉ ናቸው፡፡
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የጋዜጠኞች ቡድን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአደረጃጀት ክፍል ኀላፊ ጋሻው መርሻ በተከዜ ግንባር አነጋግሯቸዋል። አቶ ጋሻው በተከዜ ግንባር የተገኙት በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው በመግባት የወገን ጦር ባበረታቱበት ወቅት ነበር። አቶ ጋሻው እንዳሉት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በተለያዩ አካባቢዎች ወረራ ቢፈጽምም በአጭር ጊዜ ውስጥ “ይደመሰሳል ብለዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በሀሰት ፕሮፖጋንዳ ባደረገው ወረራ ያሸነፈ የመሰላቸው አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት ለቡድኑ ወግነው ቢሰሩም ድባቅ እየተመታ በመሆኑ ሀፍረትን ተከናንበዋል ነው ያሉት። አኹን ላይ ጠላት በወገን ጦር ርብርብ እየተቀጠቀጠ በመሆኑ “ወደ ጉድጓድ ለመመለስ መንገዷ የጠፋባት አይጥ” ሆኗል ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ጋሻው “ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ቆራጥ መሪዎቿና ልጆቿ አፍራሾቿን እያፈረሷቸው ነው” ብለዋል። ትግሉ እንዲፋጠን በየግንባሩ ያለው የሕዝብ ተሳትፎ የሚደነቅ መኾኑንም አቶ ጋሻው ጠቁመዋል።
የህልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ የሕዝቡ ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ነው ያሳሰቡት። አቶ ጋሻው እንዳሉት ጠላትን ለመደምሰስ የሚደረገው ትግል ሳይላላ በጋለ ስሜት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ- ከተከዜ ግንባር
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleመምህራንና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ።
Next article“ኢትዮጵያ ፈርሳ የቀድሞው ኢትዮጵያዊ መባል ስለማልፈልግ ነው የህልውና ዘመቻውን የተቀላቀልኩት” አትሌት ሻለቃ ኀይሌ ገብረ ሥላሴ