መምህራንና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ለአንድ ሳምንት በማህበራዊ አገልግሎት ይሰማራሉ።

160
ሕዳር 27/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በመላው ኢትዮጵያ የሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ዝግ ኾነው መምህራንና ተማሪዎች በተለያዩ ሥራዎች ሕዝባቸውን እንዲያግዙ ትምህርት ሚኒስቴር መወሰኑ ይታወሳል።
ይህንን ውሳኔ ተከትሎ መምህራን እና ተማሪዎች ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሥራ ይሰማራሉ።
ሰብል መሰብስብ፣ በግንባር ለወገን ጦር ድጋፍ ማሰባሰብ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ማገዝ እና ደም መለገስ የዘመቻው አካል ነው።
ተማሪዎችና መምህራን አቅማቸው በሚፈቀድውና በሚችሉት መልኩ ሕዝባቸውን ለአንድ ሳምንት ያገለግላሉ።
የበጎ ፍቃድ የዘመቻ ሥራው በኹሉም ክልሎች የሚደረግ ሲሆን የሁለተኛ ደረጃ መምህራንና ተማሪዎች እንደሚሳተፉ ከትምህርት ሚኒስቴር የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleበሎስ አንጀለስ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የሚውል 640 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ።
Next article“ኢትዮጵያ እንዳትፈርስ ቆራጥ መሪዎቿና ልጆቿ አፍራሾቿን እያፈረሷቸው ነው” አቶ ጋሻው መርሻ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የአደረጃጀት ክፍል ኀላፊ