ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ድባቅ ለመምታት ሁሉም በአንድነት መቆም እንደሚገባው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ገለጹ፡፡

152
ጎንደር፡ ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “የአንድነት ደወል ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ሐሳብ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ታላቅ የንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
በጎንደር ከተማ አስተዳደር የሰላምና ደኅንነት የህልውና ዘመቻ አስተባባሪ ኮሚቴ ከባለሀብቶች ጋር በመተባበር በተዘጋጀው የምክክር መድረክ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ መላኩ አለበል፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ታማኝ በየነ እንዲሁም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ የእናት ጡት ነካሾች በፈፀሙት ወረራ ታሪካዊ ጠላት አድርገው የፈረጁትን የአማራ ሕዝብ ለማጥቃት ቢንቀሳቀሱም መጠነ ሰፊ እርምጃ እየተወሰደባቸው መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ዘውዱ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ከንቱ ምኞቱን ለማምከን ሕዝቡ እሾህ ሁኖ እየወጋው መሆኑን ገልጸዋል። የዓድዋ ድልን በዚህ ዘመን መድገም እንደሚገባ አንስተዋል።
ደጀኑ ሕዝብም የተጠናከረ ሥራ እየሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ እስካሁን በከተማው ነዋሪ ከ97 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የስንቅ ዝግጅት ተደርጓል፤ አካባቢን ከሰርጎ ገቦች ለመቆጣጠር የ24 ሰዓት የተጠናከረ ጥበቃና ክትትል እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡
አቶ ዘውዱ አሁንም በተለያየ መስክ የደጀንነት ሚናን በመወጣት ድል እንዲገኝ መሥራት ይገባል ነው ያሉት።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ሽብርተኛውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ድባቅ ለመምታት ሁሉም በአንድነት መቆም እንደሚገባው ገልጸዋል።
ጠላት የሐሰት ፕሮፖጋንዳን እንደ ትልቅ መሳሪያ በመጠቀም ሽብር ለመንዛት እና አንድነትን ለማላላት እንደሚሠራ በማወቅ መጠንቀቅ እንደሚገባም ተናግረዋል። ሰርጎ ገብነትን በጥብቅ መከታተል ግድ እንደሚልም አስገንዝበዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው ኢትዮጵያን እና ሕዝቧን መንካት በሃይማኖት አስተምህሮ ውስጥም መከልከሉን አጣቅሰው ሕዝቡ ሀገር ለማፍረስና ለመዝረፍ የመጣውን ወራሪና አሸባሪ ቡድን #ለመደምሰስ በሁሉም ግንባር መታገል እንደሚገባው አሳስበዋል።
በአማራ ክልል የሚገኙ ባለሀብቶች አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የአማራ ብሎም የኢትዮጵያ ስጋት አለመሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ ማንኛውንም ድጋፍ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት በተወካያቸው በአቶ ተካ አስፋው በኩል አስታውቀዋል፡፡
ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ታሪካዊ ጠላት መሆኑን በማመን በተለይ የፀጥታ መዋቅሩን በሚገባ በመደገፍ ማጠናከር እንደሚገባ አንስተዋል፡፡ የኢትዮጵያን እና የአማራን ህልውና በትግላችን እናረጋግጣለን ሲሉም ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ፍፁምያለምብርሃን ገብሩ -ከጎንደር
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በወሎ ግንባር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረገ።
Next articleበመስኖ ልማት ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ለማድረግ የክልሉ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ገለጹ፡፡