
ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በወሎ ግንባር ለሚገኘው የወገን ጦር የደረቅ ሬሽንንና የአልባሳት ድጋፍ አድርጓል። ፕሮጀክቱ ያደረገው ድጋፍ ለሁለተኛ ጊዜ ነው።
ድጋፉን ያስረከቡት የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሄኖክ በለጠ ከአሁን ቀደም በጋሽና ግንባር ተገኝተው ድጋፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል። በመካነ ሰላም ተገኝተው ያደረጉት ድጋፍ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የደረቅ ምግብና የአልባሳት ድጋፍ መሆኑን ነው የገለጹት።
የሕልውና ዘመቻው ከተጀመረ ጊዜ ጀምሮ የፕሮጀክቱ ሠራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች የወር ደመወዛቸውን ከመስጠት በተጨማሪ ሌሎች ድጋፎችን ማድረጋቸውንም ነው የተናገሩት።
የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት እስካሁን ከ 6 ነጥብ 7 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ገልጸዋል።
የሕልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ፣ የተፈናቀሉ ወገኖች ወደ ቀደመ ሕይወታቸው እስኪመለሱ ድረስ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የግንባሩ የሎጅስቲክ ሰብሳቢ አቶ ተስፋ ዳኘው
የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
ሌሎች ድጋፍ የሚያደርጉ ተቋማትና ባለሀብቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation