የልዩ ዘመቻ ኃይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል ኮማንዶዎችን አስመረቀ።

285
ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የልዩ ዘመቻ ኃይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል ኮማንዶዎችን አስመርቋል።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ርእሰ መሥተዳድር ርስቱ ይርዳው ለተመራቂዎቹ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድሩ እንዳሉት ወቅቱ ጀግናው የመከላከያ ኃይላችን ከሌሎች የጸጥታ አካላትና ለነፃነት ከተመመው ሕዝባዊ ሠራዊት ጋር በመሆን እና በጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)የተቀናጀ አመራር አንፀባራቂ ድል እየተመዘገበ የሚገኝበት መሆኑ ለየት ያደርገዋል፡፡ የድሎቻችን ሚስጥር የጀግናው የመከላከያ ኃይላችን ብቃት ፣ የጸጥታ ኃይሎችና የኢትዮጵያውያን ኅብረትና ጠንካራ አንድነት ነው ብለዋል፡፡
“ወጣቶች የጀግንነት ታሪካችንን ማስቀጠል እንዲቻል ከሁሉ የላቀ ክብርና ሞገስ ወደሚያላብሰው የመከላከያ ሠራዊት ለመቀላቀል እያሳዩት ያለውን መነሳሳትና አለሁ ባይነት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው” ነው ያሉት፡፡
የመከላከያ የኅብረት መረጃ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ በቀለ ” ወቅቱ ባንዳው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሽሽት ላይ ያለበትና መላው ሠራዊታችን ግብዓተ መሬቱን ለማፋጠን #እያሳደደ አኩሪና አንፀባራቂ ድል እያስመዘገበ ባለበት ጊዜ በመሆኑ በፍጥነት ወደተመደቡበት ክፍል በመቀላቀል አሸባሪውን ቡድን #በመቅበር የድርሻችሁን መወጣት ይጠበቅባችኋል” ሲሉ አሳስበዋል፡፡
የልዩ ዘመቻ ኃይሎች ማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ኮሎኔል ዋለልኝ ታደሰ የ37ኛ ዙር ተመራቂ ኮማንዶዎቹ ማንኛውንም የሰው ሰራሽና የተፈጥሮ መሰናክሎችን በቀንና በሌሊት በማለፍ ግዳጃቸውን ለመወጣት የሚያስችል ስልጠና እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።
በተጨማሪም ወቅቱ የሚጠይቀውን ግዳጅ ለመወጣት የሚያስችል የቴክኖሎጂ ፣ ሞራላዊና ሥነልቦናዊ ስልጠናዎች በአጥጋቢ ሁኔታ መውሰዳቸውን አረጋግጠዋል።
ተመራቂዎችም ለኢትዮጵያ ክብርና አንድነት እየተካሄደ ባለው የህልውና ትግል የበኩላቸውን እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article❝ኢትዮጵያ ማለት ሲነኳት ማንም የማያውቀውን ኃይሏን የምታወጣ ሀገር ናት❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በወሎ ግንባር ለወገን ጦር ድጋፍ አደረገ።