በሁመራ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ለዘማቾች ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን እያረጋገጡ ነው።

174
ሁመራ: ሕዳር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በሁመራ ከተማ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ለወገን ጦር ስንቅ በማዘጋጀት የደጀንነት ኀላፊነታቸውን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ለአማራ ሚዲያ ኮርፓሬሽን (አሚኮ) ተናግረዋል።
ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን የከፈተውን ወረራ ለመመከት የመንግሥት የክተት ጥሪን በመቀበል መዝመት የሚችሉ የመንግሥት ሠራተኞች ወደ ግንባር ዘምተዋል። መዝመት ያልቻሉት ደግሞ አሸባሪውንና ወራሪውን የትግራይ ቡድን ድባቅ እየመታ ለሚገኘው የወገን ጦር ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን እያረጋገጡ ይገኛሉ።
ስንቅ ሲያዘጋጁ ካገኘናቸው መካከል ገነት ፍታለሁ አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ቡድን ለመደምሰስ ለዘመተው የወገን ጦር ስንቅ በማዘጋጀት ላይ ነን ብላለች።
አሸባሪው ቡድን ከምድረ ገፅ #እስኪወገድ ድረስ ስንቅ በማዘጋጀትና ግንባር ድረስ በመዝመት ስንቅ ለማቀበል ዝግጁ መሆኗንም ገልፃለች።
የሁመራ ከተማ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽሕፈት ቤት ባለሙያ አቶ ተከታይ ረዳ የወገን ጦር በግንባር እያስመዘገበ ያለው ድል የሚደነቅ ነው ብለዋል። ደጀንነታቸውንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን #እስካልተደመሰሰ ድረስ ሰላም ማግኘት እንደማይቻል የገለፀችው የቴክኒክና ሙያ ኢንተርፕራይዞች የሥራ እድል ፈጠራ ባለሙያ እየሩስ ኃይለ ሥላሴ እየተገኘ ያለውን ድል ለማስቀጠል ለወገን ጦር ስንቅ በማዘጋጀት እና ሁለንተናዊ ድጋፍ በማድረግ እየተሳተፈች መሆኗን ተናግራለች።
አመርቂ ድልን ለመጎናፀፍ የሕዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ወጣቱ መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል አቅም ያለው ወደ ግንባር በመዝመት፣ መዝመት ያልቻለም ስንቅ በማዘጋጀት ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ሠራተኞቹ ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ- ከሁመራ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“በዘመቻ ለ‘ኅብረ ብሔራዊ አንድነት’ የኢትዮጵያ አሸናፊነት ይረጋገጣል” አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ
Next article❝ኢትዮጵያ ማለት ሲነኳት ማንም የማያውቀውን ኃይሏን የምታወጣ ሀገር ናት❞ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)