“በዘመቻ ለ‘ኅብረ ብሔራዊ አንድነት’ የኢትዮጵያ አሸናፊነት ይረጋገጣል” አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ

135
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ለኢትዮጵያ አሸናፊነት የአራቱም ማዕዘናት ልጆቿ ብርቱ የአንድነት ንቅናቄ ጉልህ ድርሻ እንዳለው
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ተናግሯል።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በአፋር ክልል በመገኘት በአሸባሪው የህወሃት ወራሪ ኃይል ከጭፍራ ከተማ ተፈናቅለው ለሰብዓዊ ቀውስ ለተጋለጡ ዜጎች የሚውል ድጋፍ አበርክቷል።
ከመኖሪያ ቀዬአቸው ተፈናቅለው በሃምሳ ጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮችናንና በሽብር ቡድኑ ውድመት የደረሰበትን የጭፍራ ከተማ ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ወቅት እንደገለጸው፤ በጭፍራ ከተማ መገኘቱ ሁለት አይነት ተቃራኒ ስሜት ፈጥሮበታል።
ይኸውም የወገን ጦር በሽብር ቡድኑ ወራሪ ኃይል ላይ የተቀዳጀው አንጸባራቂ ድል እንዳኮራውና በተቃራኒው አሸባሪው ቡድን በወረራ በቆየባቸው ጊዜያት በዜጎች ህይወትና በንብረታቸው ላይ ያደረሰው ዝርፊያና ውድመት ደግሞ አሳዛኝና ልብ ሰባሪ እንደሆነ ገልጿል።
የሽብር ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች ከተማዋን ለማውደም የፈፀሙት ጥፋት ሞራለቢስነት የተሞላበት እንደሆነም አንስቷል።
የክፋት ሁሉ ባለቤት የሆነውን የህወሃት የሽብር ቡድንን ጥፋት የሚሰማና የሚመለከት የትግራይ ህዝብም በቃህ ሊለው እንደሚገባም አስገንዝቧል።
የሽብር ቡድኑን የጥፋት ጉዞ በመግታት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፣ የአፋር ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻና ህዝቡ እያደረጉት ያለው አኩሪ ተጋድሎ የሚደነቅ እንደሆነም ገልጿል።
በዘመቻ ለ‘ኅብረ ብሔራዊ አንድነት’ ኢትዮጵያዊያን መስዋእትነቶችን ከፍለው ኢትዮጵያን አሸናፊ እንደሚያደርጓት ተናግሯል።
ወራሪው ቡድን በጭፍራና ካሳጊታ ከተሞች ቤተ እምነቶችን በማውደም ቅዱስ ቁርዓንን ጨምሮ ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትን ማቃጠሉ እንዳሳዘነውም ጠቅሷል።
በቀጣይም ኢትዮጵያዊያን ያላቸውን በማካፈል፣ የወደሙ ቤተ እምነቶችንና መሰረተ ልማቶችን በመገንባትና ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በመድረስ ጉዳት የደረሰበትን ህዝብ መልሶ ማቋቋም ይገባል ሲልም ጥሪ አቅርቧል።
በግንባር ተሰልፈው ጠላትን አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስቀጠል የህይወት መስዋእትነት እየከፈሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የኢትዮጵያን ከፍታ እንደሚያረጋግጡ ጥርጥር የለኝም ብሏል።
ለሰራዊቱ ቤተሰቦች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ደግሞ የኢትዮጵያዊያን ሁሉ የቤት ስራ ሊሆን እንደሚገባም ገልጿል።
አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በ”ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በመደገፍ በየአውደ ግንባሩ እየተገኘ የሀገር አለኝታነቱን በማረጋገጥ ላይ የሚገኝ ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ ነው ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleሕዝቡ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን በወሎ ግንባር የወገን ጦር አባላት ተናገሩ።
Next articleበሁመራ ከተማ የመንግሥት ሠራተኞች ለዘማቾች ስንቅ በማዘጋጀት ደጀንነታቸውን እያረጋገጡ ነው።