
ሕዳር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ኃይል በኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያውያን ጦርነት ከፍቷል። ንፁሐንን በግፍ ገድሏል። አፈናቅሏል ሀብትና ንብረታቸውንም አውድሟል። የሽብር ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት የኢትዮጵያ የቁርጭ ቀን ልጆች እያመከኑበት ነው። የሽብር ኃይሉንም እየደመሰሱ ይዟቸው ከነበሩ አካባቢዎች እያፀዱት ነው። ሠራዊቱ በጀግንነት እንዲዋጋ የሕዝቡ ደጀንነት ከፍተኛ መሆኑንም የሠራዊት አባላቱ ተናግረዋል።
የአማራ ልዩ ኃይል አባል የሎጅስቲክ አስተባባሪ ማኅበረሰቡ የስንቅ አቅርቦቱን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል። ሕዝቡ የሚያቀርበውን ስንቅ በአንድ ማዕከል በማድረግ እያደረሱ መሆናቸውንም አስታውቀዋል። ማኅበረሰቡ የሚያደርገው ድጋፍ ለሠራዊቱ ከፍተኛ ሞራል እየሆነው መሆኑንም ገልፀዋል።
ሠራዊቱ ጠላትን እየመታ ወደ ፊት በሄደ ቁጥር ማኅበረሰቡ ውኃ፣ እንጀራ፣ ቆሎ፣ ዳቦና እሸት ሳይቀር እያቀረበ ሠራዊቱ ለሌላ ድል እንዲገሰግስ እያደረገው እንደሚገኝም ተናግረዋል። የሕዝቡ አቅርቦት ደስ የሚያሰኝ አለኝታና መከታ መሆኑን እያስመሰከረ እንደሆነም ገልፀዋል። መኪና በማይገባበት አካባቢ ማኅበረሰቡ በሸክምና በጋማ ከብቶች እየጫነ ምሽግ ድረስ ለሠራዊቱ እያቀረበ መሆኑንም ተናግረዋል።
የአማራ ሕዝባዊ ኃይል ፋኖ የሎጅስቲክ ኃላፊም የሕልውና ዘመቻው ከጀመረ ጀምሮ የባለሀብቶችና የመላው ሕዝብ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀዋል። የደጀኑ ሕዝብ ተሳትፎ የሚደነቅ መሆኑንም አንስተዋል።
የሚሊሻ የሎጅስቲክ አስተባባሪውም ሕዝቡ ለሠራዊቱ አስተማማኝ የኋላ ደጀን መሆኑን ተናግረዋል። ሠራዊቱ የሕልውና ዘመቻን በአጭር ጊዜ እንዲያጠናቅቅ ድጋፉ ላቅ ያለ እንደሆነም ገልፀዋል። ሕዝቡ ያለውን ሁሉ ለሠራዊቱ እየላከ መሆኑንም አንስተዋል።
የግንባሩ የሎጅስቲክ ሰብሳቢም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልፀዋል። ሕዝቡ የሚያመጣውን ድጋፍ በአንድ ማዕከል በማከማቸት ወደ ምሽጉ በፍትሐዊነት እየተዳረሰ መሆኑንም ገልፀዋል። የሕዝቡ ድጋፍ አበረታች፣ መንግሥት ከሚያቀርበው የላቀ የሆነና ለሠራዊቱ ከፍተኛ ሞራል የሆነ ነውም ብለዋል። የሚቀርበው ድጋፍ በፍትሐዊነት የሚዳረስ መሆኑን አውቀው ዜጎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:-ታርቆ ክንዴ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation