“የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን መሪዎች የትግራይን ወጣት እሳት ወደኾነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት እየማገዱት ነው” አርቲስት ታማኝ በየነ

390
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ታማኝ በየነን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎች፣ ባለሀብቶችና የሃይማኖት አባቶች በተከዜ ግንባር በመገኘት ለወገን ጦር ድጋፍ አድርገዋል።
የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ዓላማ እናት ኢትዮጵያን ማፍረስ፣ የአማራን ሕዝብ ማንበርከክና የአማራን ሕዝብ በመውረር ሀብትና ንብረት መዝረፍ፣ ማውደም ነው ብለዋል። አቶ መላኩ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራዎችና ባለሀብቶች ለዘመቻው እያደረጉት ላለው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የማኅበራዊ አንቂና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አርቲስት ታማኝ በየነ በግንባሩ ለተሰለፈው ኀይል ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ስለ ኢትዮጵያ አንድነትና ጀግንነት ንግግር አድርጓል፡፡
“በውጭ ሀገራት የምንኖረው ኢትዮጵያውያን ግንባር ድረስ የተገኘነው እናንተ የሀገር አለኝታ ከኾናችሁት ጎን መኾናችንን ለማሳየት ነው” ብሏል። ኹሉም ኢትዮጵያዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ጀብድ የሚያንጸባርቅ ንቅሳት ይነቀሳልም ብሏል።
የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል መሪዎች የትግራይን ወጣቶች እሳት ወደኾነው የሀገር መከላከያ ሰራዊት #እየማገዱት መኾኑን የጠቆመው አርቲስት ታማኝ የሽብር ቡድኑ አባላት እጅ እንዲሰጡ ጠይቋል።
“ለኢትዮጵያ ብላችሁ ደማችሁን ያፈሰሳችሁ፣ አጥንታችሁን የከሰከሳችሁ የወገን ኀይሎች ኹሉ ታሪካችሁ ሲዘከር ይኖራል። እንወዳችኋለን፣ እናከብራችኋለንም” ነው ያለው።
የወገን ኀይልን ለማበረታት ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት ውስጥ አንዱ ዲያስፖራ ነዓምን ዘለቀ ናቸው። ዲያስፖራው ባደረጉት ንግግር የትግራይ ወራሪ ኀይል የኢትዮጵያ ስጋት በማይኾንበት ሁኔታ ላይ ለማድረስ መቀበር አለበት ብለዋል። የወገን ጦር በተባበረ ክንዳችሁ አሸባሪውን ቡድን እንደምትቀብሩት አልጠራጠርም ብለዋል።
በውጪ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በኹሉም ተግባር ከወገን ኀይል ጎን እንደሚሰለፉ አረጋግጠዋል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ያለዓለም ፈንታሁን አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በሰሜን ጎንደር ዞን ወረራ ቢፈጽምም በተባበረ የወገን ኀይል ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶበት ቅስሙ የተመታበት አካባቢ ነው ብለዋል።
የአካባቢው ማኅበረሰብ የአባቶቹን ታሪክ የጠበቀ፣ የአባቶቹን ታሪክ የሚያወራ ብቻ ሳይኾን ታሪኮቹን በጀግንነት ያስቀጠለ መኾኑን ዋና አስተዳዳሪው ገልጸዋል። አቶ ያለዓለም እንዳሉት የአካባቢው ማኅበረሰብ ትግል እየተካሄደ ትኩስ ስንቅ በማዘጋጀት ሞራል ሲሰጥ ቆይቷል።
ሌላው ባለሀብቶችን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ ተካ አስፋው ባለሀብቱ ድርጅቱን በመዝጋት በየግንባሩ ስንቅ በማዘጋጀት የወገን ኀይልን ሲያበረታታ ቆይቷል እያበረታታም ይገኛል ብለዋል። ድጋፍ ማድረግ ብቻ ሳይኾን ግንባር በመገኘት ጠላትን ለመደምሰስ ዝግጁ መኾናቸውንም ነው ተወካዩ የተናገሩት።
ዘጋቢ:- ቡሩክ ተሾመ-ከተከዜ ግንባር
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየህልውና ዘመቻውን ለመደገፍ ከ3 ቢሊየን 320 ሚሊየን በላይ ገንዘብ መሰብሰቡን የአማራ ክልል የህልውና ዘመቻው አሰባሳቢ ግብረ ኀይል አስታወቀ።
Next articleሕዝቡ ለሠራዊቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠሉን በወሎ ግንባር የወገን ጦር አባላት ተናገሩ።