
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ባለበት የዓለም ሀገር ሁሉ ስለ ኢትዮጵያ እውነት ንቅናቄ ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለጹት የመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ ይህም በቀላሉ የማይታይ ታላቅ ተጋድሎ ነው ብለዋል፡፡
ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ ላይ የያዘው የተሳሳተ ግንዛቤ የሚቀረፈው በሁሉም ጥረት እንደሆነ የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ በሚቀጥለው የገና በዓል አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ኢትዮጵያ በመገኘት እውነታውን ለዓለም እንዲያስረዱ ጠይቀዋል፡፡
የንቅናቄውን ሀሳብ ያመነጩት ምስጋና እንደሚገባቸውም አንስተዋል፡፡ “እኛ ኢትዮጵያውያን ለሀገራችን አናንስም” በሚል የተጀመረው ንቅናቄ ፍሬ እንዲያፈራም የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እቅድ አውጥተው እየተንቀሳቀሱ ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ወቅት እያደረጉት ያለው የጋራ ጠላትን የማጥፋት ርብርብ በቀጣዩ ተውልድ በታሪክ ሲዘከር እንደሚኖርም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
በደጀን አምባቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation