“ቃርሚያ መልቀም”

168
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአሁ ወቅት አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በጀግናው የወገን ጦር እየተደመሰሰ ሸዋ ምድር ከወራሪው የትግራይ ቡድን ጸድቷል። በወሎም በርካታ ወረዳዎችና ከተሞች ነፃ ወጥተዋል።
የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኀይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አሕመድ ጀግናውን የመከላከያ ሠራዊት እና ሁሉንም የፀጥታ ኀይሎች እየመሩ ወደተቀናጀ የማጥቃት ርምጃ ከተገባ በኋላ አሸባሪው ቡድን ድንብርብሩ ወጥቷል።
አሸባሪው ቡድን የጀግናውን የወገን ጦር የተቀናጀ እና የተናበበ ጥቃት መመከት ባለመቻሉም ለወራት የገነባቸውን ጠንካራና የተማመነባቸውን ምሽጎች፣ ታንኮች፣ መድፎች፣ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች እና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችን ጥሎ ከመፈርጠጥ ባለፈ በየግንባሩ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል።
ከቅጥረኞቹ ኦነግ ሸኔና የጉሙዝ ታጣቂ ጋር ተዋግቼ ሚሌን እና አዲስ አበባን እቆጣጠራለሁ ሲል የነበረው አሸባሪ ቡድን ዛሬ ብቸኛ ምርጫው ወይ እጅ መስጠት ካልሆነም እንደቅጠል መርገፍ ብቻ ሆኗል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሰሞኑን ከግንባር ሆነው ባስተላለፉት ቁልፍ መልእክት የሽብር ቡድኑ አባላትን እጅ ስጡ ብለዋቸዋል። በርካቶችም ጥሪውን ተከትሎ በተለያዩ ግንባሮች እጅ እየሠጡ ይገኛሉ።
ጀግናው የወገን ጦርም በዚህ ወቅት የተደነባበረውን አሸባሪ ቡድን ሙትና ቁስለኛ እያደረገ ወደፊት እየገሰገሰ ነው።
“ተበትኖብኛል ሲታጨድ ነዶዬ፣
ቃርሚያ መልቀም ሆኗል ሰሞኑን ሥራዬ።”
ይሄ የሀገሬ ገበሬ የመኸር ስራው እንደሆነ ሁሉ በዚህ ወቅት በቀየው ጠላት ለሚገኝ አርሶ አደር እና ከተሜ በኢትዮጵያ መንግስት የተላለፈ ጥብቅ መልእክት ነው።
ጠላት ተሸንፎ በተስፋ መቁረጥ ጉዳት እንዳያደርስብህ በየቀየህ ተደራጅተህ የተበታተነውን የአሸባሪ ቃርሚያ ልቀም ተብሏልና።
ባለቅኔው ሙሐዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረትም ይህንን ቁልፍ የደኅንነት ተግባር በተመጠኑ ቃላት ሲገልፁት የዛሬው ቀን “”ቃርሚያ መልቀም” ይባላል ብለዋል።
በሀብተጊዮርጊስ አበይ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየጋሸና የጨለማ ወራት…
Next articleየዳንሻ ከተማ አስተዳደር ወጣቶች አካባቢያቸውን ተደራጅተው በንቃት እየጠበቁ ነው።