አዲስ አበባ በአንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት መገናኛ ብዙኃን እንደሚወራው ሳይሆን ሰላሟን አረጋግጣ የቀጠለች ከተማ ናት ሲሉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር አውሮሊያ ካርባሎ ተናገሩ።

106
ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሰባተኛው የመላው አፍሪካ የቆዳ ትርኢትና የፋሽን ምንጭ ሳምንት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር አውሮሊያ ካርባሎ ሰባተኛው የመላው አፍሪካ የቆዳ ትርዒትና የፋሽን ምንጭ ሳምንት ኤግዚቢሽን ላይ እንደገለጹት፣ አዲስ አበባ በአንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት መገናኛ ብዙኃን እንደሚወራው ሳይሆን ሰላማዊ ከተማ ናት።
ኤግዚቢሽኑ ሰላማዊና ውብ ከተማ በሆነችው አዲስ አበባ እየተካሄደ ነው ያሉት ዳይሬክተሯ የአፍሪካን ንግድና የንግድ እንቅስቃሴ በሚገባው ልክ ማሳደግ ይገባል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
የመላው አፍሪካ የቆዳ ትርዒትና የፋሽን ምንጭ ሳምንት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል መከፈቱ ይታወሳል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በጤና ተቋማት ባደረሰው ውድመት 19 ሰዎች ሕክምና አጥተው ሕይወታቸው ማለፉን የአምደወርቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ገለጸ።
Next articleየጋሸና የጨለማ ወራት…