አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ገነቴ ከተማ በንጹሃን ላይ ግድያ፣ በንብረት ላይ ውድመት ሲፈጽም እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ።

389
ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪው ቡድን ከገነቴ ከተማ ተደብድቦ ሲወጣ መሠረተ ልማቶችን አውድሞ ነው የሸሸው። ለቀናት በገነቴ ከተማ የቆዬው አሸባሪው የትግራይ ወራሪው ቡድን በወገን ጦር በደረሰበት ከፍተኛ ምት ገሚሱ ሲደመሰስ ገሚሱ ደግሞ መሠረተ ልማቶችን እያወደመ ሸሽቷል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሥፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በባንኮች፣ በጤና ተቋማት እና በሌሎች የሕዝብ መገልገያ ተቋማት ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል። የቻለውን የግለሰብና የመንግሥት ሀብት ዘርፎ ሲሸሽ ማውጣት ያልቻለውን ደግሞ ውድመት አድርሶበታል።
በነዋሪዎች ላይ የተለያዩ በደሎችን ፈፅሟል። ንጹሃንን ገድሏል፤ ገንዘብ ቀምቷል፤ ደብድቧል፤ የሚበላ አምጡ በማለት አሰቃይቷል። እንደ ከተማዋ ነዋሪዎች ገለፃ ከሆነ በከተማዋ ከፍ ያለው ሀብት ብቻ ሳይሆን ዶሮና እንቁላል እየፈለጉ እየወሰዱ ይበሉባቸው ነበር።
አስተያየት የሰጡን የከተማዋ ነዋሪ መሐመድ አሊ አሸባሪው የትግራይ ወራሪው ቡድን ከተማዋን እስኪበቃው ድረስ ዘርፏል፤ አውድሟል ነው ያሉት። በቤታቸው ውስጥ የነበረን ሀብት ዘርፈው የቀረውን አውድመው መሄዳቸውን ነው የተናገሩት። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አባላት የአንገትና የጆሮ ጌጥ እያስወለቁ፣ ኪስ ሳይቀር እየፈተሹ መዝረፋቸውንም ገልፀዋል።
የከተማዋን ነዋሪዎች ጥቆማ ስጡ እየተባሉ ሲሰቃዩ መሰንበታቸውንም ተናግረዋል። አስተያየት ሰጪው የወገን ጦር እስከሚደርስላቸው ድረስ በጭንቀትና በመከራ መሠንበታቸውን ገልፀዋል። በከተማዋ ሱቆችንና ቤቶችን እየሰበሩ በርብረው መውሰዳቸውንም ተናግረዋል።
ሌላኛው የከተማዋ ነዋሪ ተስፋ አህመድ የአሸባሪው ቡድን አባላት እያስፈራሩ እንደዘረፏቸው ነግረውናል። አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘር ለማጥፋት የመጣ መሆኑንም ገልፀዋል።
በተደጋጋሚ ሊገድሏቸው ሲያስፈራሯቸው እንደነበርም ገልፀዋል። የወገን ጦር በጭንቅ ቀን እንደደረሰላቸውም ተናግረዋል። የወገን ጦር በሚያስደንቅ ጀግንነት እንደቀጠቀጣቸውም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“ለፍትሕ፣ ለነጻነታችን፣ ለክብራችን፣ ሀገራችንን ለመጠበቅ እንፋለማለን” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ
Next articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ “ወደ ሀገር ቤት እንግባ” ጥሪን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አጋር ኾኖ ለማስተባበር ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ።