“ለፍትሕ፣ ለነጻነታችን፣ ለክብራችን፣ ሀገራችንን ለመጠበቅ እንፋለማለን” አቶ ተመሥገን ጥሩነህ

291
ሕዳር 24/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል ተመሥገን ጥሩነህ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በመልዕክታቸውም “ለፍትሕ፣ ለነጻነታችን፣ ለክብራችን፣ ሀገራችንን ለመጠበቅ እንፋለማለን” ነው ያሉት፡፡
“እነሱ እኩይ ዓላማ ይዘው ለመዝረፍ፣ ንጹሐንን ለመግደል፣ ሠራዊታችንን ለመበተን እና ሀገር ለማፍረስ ይዋጉናል። እኛ ደግሞ ለፍትሕ፣ ለነጻነታችን፣ ለክብራችን፣ ሀገራችንን ለመጠበቅ እንፋለማቸዋለን። እናም የእነሱ ሞት ዓላማ ቢስ ከንቱ መስዋእትነት ሲሆን የእኛ ደግሞ የሀገርን እና የሕዝብን የቆዬ የአይደፈሬነት ክብር አስጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚከፈል ዘመን ተሻጋሪ እና ታሪካዊ ክቡር መስዋእትነት ነው” ብለዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሰፈር እና ሀገር ባንዳዎችን አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ያለምህረት ሊፋለም እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያ በጀግኖች ልጆቿ አጥንትና ደም ተከብራ የኖረች ለወደፊቱም የምትኖር ሀገር ናት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous article“…በአንድነት ተነስተን አሸባሪዎችን ድባቅ እንመታለን” ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ
Next articleአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ገነቴ ከተማ በንጹሃን ላይ ግድያ፣ በንብረት ላይ ውድመት ሲፈጽም እንደነበር ነዋሪዎች ተናገሩ።