ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ በሳምንታዊ መግለጫቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡፡

337
ባሕርዳር፡ ሕዳር 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ)
-በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር በተደረገው የቻይና አፍሪካ የትብብር ፎረም በቻይና በኩል የቀረበው የልማት አቅጣጫ እና የሚፈጠረው አዲስ ግሪን ላይን የንግድ መስመር ኢትዮጵያን የበለጠ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ፡፡
-ኢትዮጵያ የንግድ መሥመር ምርቶቿን ያለቀረጥ የምታደርስበት መንገድ መመቻቸቱ፡፡
-የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሬድዋን ሁሴን በሴኔጋል ዳካር ተገኝተው በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ጫና ማስረዳት መቻላቸው እና የተገኘው ውጤት አበረታች መሆኑ፡፡
-ኢትዮጵያ የራሷን ችግር በራሷ መፍታት የሚያስችል አቅም፣ ችሎታ እና ስልጣኔ እንዳላት የቻይና ፕሬዝዳንት መግለጻቸው፡፡
-በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ላይ የሚደረገው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የሚጠይቀው የ ‟ኖ ሞር“ ዘመቻ ተጠናክሮ መቀጠሉ እና የተገኘው ውጤት በጎ መሆኑ፡፡
-ኢትዮጵያውያን ሀብት የማሰባሰብ ሥራቸውን አጠናክረው በመቀጠል ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚያደርጉት እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉ፡፡
-1 ሚሊየን ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በጥር ወር በሚከበሩ በዓላት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው እንዲጎበኙ ሁኔታዎች መመቻቸታቸው፡፡
-በመንግሥት የተፈጸመ የዘር ማጥፋትም ሆነ ረሀብን እንደ ጦር መሣሪያ ማዋል እንደሌለ መረጋገጡ እና የኢትዮጵያ መንግሥት እና የተባበሩት መንግሥታት ከፍተኛ የሰባዊ መብት ጥሰት ኮሚሽን ጽሕፈት ቤት ይህንኑ ማረጋገጣቸው፡፡
-የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰብዓዊ መብት መከበር ያለውን የጸና አቋም ለማሳየት ግብረኀይል ተቋቁሞ እየሠራ መሆኑ፡፡
-በሌላ ወገን የሚደረገውን ጭፍጨፋ ከቁብ ባለመቁጠር የሰብዓዊ ጥሰት እየተፈጸመ ነው በሚል የሚጮሁ መገናኛ ብዙኃን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጥሪ መቅረቡ፡፡
-ኢትዮጵያ ሰላሟ ተናግቷል እያሉ የሚያወሩ አንዳንድ ኢምባሲዎች ከአሉባልታ ወሬያቸው እንዲታቀቡ እና ኢትዮጵያን መጎብኘት፤ ከኢትዮጵያ ጋር መሥራት የሚፈልግ ማንኛውም አካል መምጣት እንደሚችል ሊረዳ እንደሚገባ መገለጹ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡-ትርንጎ ይፍሩ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleትውልደ ኢትዮጵያዊው ኦባላ ኦባላ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የፈጸመውን እና እየፈጸመ ያለውን ግፍ ለአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን ማስረዳቱን ገለጸ፡፡
Next article❝የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ችግር በራሷ የመፍታት አቅም እንዳላት መገንዘብ መቻላቸው ትልቅ የዲፕሎማሲ ስኬት ነው❞ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ