
ጎንደር: ሕዳር 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዳሽን ቢራ ፋብሪካ ለህልውና ዘመቻው 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብና 200 ኩንታል ዱቄት ድጋፍ አድርጓል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ የሰው ኃይል መምሪያ ሥራ አስኪያጅ አቶ ነጋ አምባው ከፋብሪካው በጥሬ ገንዘብ 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብርና ለደረቅ ሬሽን ዝግጅት የሚሆን ሁለት መቶ ኩንታል ዱቄት ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል።
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ ፋብሪካው እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚበረታታ ነው ብለዋል።
የዳሽን ቢራ ፋብሪካ ከሠራተኛ ማኅበሩ ለሁለተኛው ዙር የክተት ጥሪ ከ1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የዓይነት ድጋፍ በጠለምት ግንባር ድጋፍ መደረጉን የሰው ኃይል መምሪያ ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል።

የዳሸን ቢራ ፋብሪካ ለህልውና ዘመቻው እስካሁን ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ:- ጳውሎስ አየለ- ከጎንደር