
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወገን ጦር የደረሰበትን ከፍተኛ ምት መቋቋም ተስኖት በፈንጂዎች ያጠረውን ኮንክሪት ምሽግ ጥሎ ፈርጥጧል። ጠላት በደረሰበት ድንጋጤ የአባላቱን አስከሬን እንኳን ማንሳት እንዳልቻለ በስፍራው ተገኝተን ተመልክተናል።



የወገን ጦር እየወሰደ ባለው ርምጃ የጠላት መጠቀሚያ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች የወደሙ ሲኾን መድፈኛ ታንኮች ከነተተኳሻቸው ተማርከዋል። የማጥቃት ርምጃውን መቋቋም የተሳነው ጠላትም በርካታ ልዩ ልዩ ተተኳሽ ጥይቶችን እያንጠባጠበ ነው የፈረጠጠው።
የአሚኮ የጋዜጠኞች ቡድን በግንባሩ ተገኝቶ እንደተመለከተውም የወገን ጦር በከፍተኛ የጀግንነት ወኔ ጠላትን ድባቅ እየመታው ይገኛል።


ዘጋቢ :- ደጀኔ በቀለ– ከጋሸና ግንባር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation