
ባሕርዳር፡ ሕዳር 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል። ዶክተር ይልቃል መንግሥት ላቀረበው የክተት ጥሪ ከሕዝቡ የተሰጠው ምላሽ ፈጣን እና አበረታች በመሆኑ ምስጋና አቅርበው የሕልውና ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።
እየተመዘገበ ያለው ድል የመላዉ ኢትዮጵያዊያን መሆኑንም ገልጸዋል። መንግሥት እየወሰደ ባለው የማጥቃት እርምጃ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በሁሉም ግንባሮች እየተደመሰሰ መሆኑን የገለጹት ርእሰ መስተዳድሩ ሕዝቡ ከጸጥታ ኅይሉ ጋር በመቀናጀት ይህንን ዘራፊ እና ጨፍጫፊ ቡድን እንዲቀብረው ጥሪ አስተላልፈዋል።
ርእሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል እንዳሉት አንድም የሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን አባል ከወረራቸው አካባቢዎች አምልጦ እንዳይወጣ ሕዝቡ መንገዶችን በመዝጋት እንዲደመስሰው፤ የዘረፋቸው ንብረቶች እንዳይወጡ በንቃት መከታተል እና ማስጣል አለበት።
የሀገርን ሉዓላዊነት በዘላቂነት ለማስከበር ወጣቱ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና ልዩ ኅይልን እንዲቀላቀልም ዶክተር ይልቃል ጥሪ አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- የማነብርሃን ጌታቸው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation