
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 22/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሩሲያ ከመጀመሪያውም በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የምዕራባዊያን ጣልቃ ገብነት እንዳይኖር አስጠንቅቄያለሁ አለች።
በተባበሩት መንግሥታት የሩሲያ ፌደሬሽን ተልዕኮ ተቀዳሚ ምክትል ተጠሪ ዲሚትሪይ ፖለንስኪይ “ከጅምሩ ምዕራባዊን ወዳጆቻችን በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡና ግልፅነት በጎደለው አካሄድ ምንም ዓይነት ድርጊትን እንዳይፈፅሙ አስጠንቅቀናል” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በጦርነቱ ውስጥ የውጭ ኃያል አገራት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለ ማለቱን በማስታወስ ይሄ ጉዳይ ለኢትዮጵያዊያን እጅግ ስስብለት (ትብ ጉዳይ) መሆኑን ሩሲያ አስምራበታለች። የትኛውም አሰላለፍ ግልፅ መሆን አለበት ሲሉም በእጅ አዙርና በድብቅ ዓላማን ለማስፈፀም መሞከርን ኮንነዋል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorpo