“የውጭ ጫናዎችን ለመከላከል የሚደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ስኬት እያስመዘገቡ ነው” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

213
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ የሚደርሰውን የውጭ ጫና ለመከላከል የሚደረጉት ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ስኬት እየተመዘገበባቸው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ።
አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንደተናገሩት፤ አንዳንድ የምዕራባውያን ሀገራት በኢትዮጵያ ላይ ነባራዊ ሁኔታን ያላገናዘበ ያልተገባ ዲፕሎማሲያዊ ጫና እያደረጉ ነው።
በተለይም ሰሜኑ የሀገሪቱ አካባቢ የሕግ ማስከበር ዘመቻውን ተከትሎ ወደ ትግራይ የሰብዓዊ እርዳታ እንዲደርስ መንግሥት የሚያደርገውን ጥረት እውቅና የመንፈግ አካሄድ በስፋት እየተስተዋለ መሆኑን ጠቁመዋል።
በተጨማሪ የተፈጸሙ ኢ-ሰብዓዊ ድርጊቶችን ለማጣራትና የድርጊቱ ፈጻሚ አካላት ላይ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚያደርገውንም ጥረት ከቁብ ያለመቁጠር ሁኔታ መኖሩን ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የታላቁ ሕዳሴ ግደብን የዓለም የጸጥታ ስጋት አስመስሎ በማቅረብ የታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በመንግስታቱ ደርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ እንዲያልቅ የሚያደርጉትን ጥረትም ሌላኛው ጫና መሆኑን ገልጸዋል።
ጎን ለጎንም የሱዳን መንግሥት በሕገ-ወጥ መልኩ የኢትዮጵያን መሬት መያዙንና ይህም የኢትዮጵያን የግዛት አንድነትና የብሔራዊ ጥቅሟን የሚገዳደር የውጭ ጫና መሆኑንም ነው የተናገሩት።
እነዚህን ወቅታዊ ጉዳዮችን ተንተርሶ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረጉትን ያልተገቡ ጫናዎች ለመከላከልና ለመቋቋም የሚደረጉ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ውጤታማ መሆናቸውን አምባሳደር ዲና አብራርተዋል።
በሌላ በኩል በቅርቡ አንዳንድ ኢትዮጵያዊያን እንዲሁም የቀድሞ የአሜሪካና የምዕራብ ሀገራት ዲፕሎማቶች የተሳተፉበት ውይይት ሕጋዊ መንግሥትን ለመገልበጥ የሚደረገው ሴራ አካል መሆኑን ተናግረዋል።
ይህ አይነቱ አካሄድም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትም ሆነ በአፍሪካ ኅብረት ቻርተር አልያም ደግሞ የሀገራትን ግንኙነት በሚወስኑ ዓለም አቀፍ ሕጎች ተቀባይነት የሌለው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥትን ለመገልበጥ በሚያሴሩ የውጭ ዲፕሎማቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ለማድረግ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸው፤ ደያስፖራውም በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው ብለዋል።
በተለይም በኢትዮጵያ ላይ የሚደርሰውን የውጭ ጫና ለመከላከል የተጀመረው የ “በቃ” ንቅናቄ /No More/ ንቅናቄ ጉዳዩን አፍሪካዊ ጭምር በማድረግና ጫናውንም በመከላከል ረገድ ውጤታማ መሆኑን አምባሳደር ዲና ገልጸዋል።
በዚህ ንቅናቄ ውስጥ አፍሪካዊ ታዋቂ ሰዎች መቀላቀላቸው ኢትዮጵያ የያዘቸውን አጀንዳ የአፍሪካዊ ጉዳይ እንዲሆንና ጉዳዩ ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ ያስቸለዋልም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ጫና እና ጣልቃ ገብነት ለማስቆም የኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ትግል መጠናከር አለበት።
Next articleሰበር ዜና