“በጦርነቱ ምክንያት ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል” ትምህርት ሚኒስትር

175
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የጥፋት ኃይሉ ህወሓት በፈጸመው ወረራ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን የሚበልጡ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ መሆናቸውን ገለጹ፡፡
ከወር በፊት በነበረው መረጃ ከአንደኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚያስተምሩ ከ1 ሺህ 600 በላይ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት መድረሱንና 300 ያህሉ ሙሉ በሙሉ መውደማቸውንም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የገለጹት።
የጥፋት ቡድኑ በከፈተው ጦርነት በትግራይ ክልል የሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎችን ጨምሮ የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ስራ ማቆማቸው ይታወቃል፡፡
በእነዚህ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ያሉ ተማሪዎችንና መምህራንን ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የመመደብ ስራ እንደተሰራም ገልፃዋል፡፡
የጥፋት ቡድኑ የከፈተውን ጦርነት በአጭር ጊዜ በመቀልበስ በቀጣይ የትምህርት ስርዓት ላይ በማተኮር መስራት ያስፈልጋል ማለታቸውን የትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።
የትምህርት ሚኒስቴርም በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ወደ ቀድሞ ይዞታቸው ለመመለስ እንሚሰራ ተናግረዋል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleከጥንት እስከ ዛሬ የድል አብሪ ኮከቦች – ኢትዮጵያውያን
Next articleበኩር ጋዜጣ ሕዳር 20/2014 ዓ.ም ዕትም