
ፍኖተሰላም፡ ሕዳር 19/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሀገር ለማፍረስ ዓልሞ የከፈተውን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ውስጣዊ አንድነትን ማጠናከር እንደሚገባ የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ የህልውና ዘመቻውን በማስመልከት የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኀይል የፈጸመውን ወረራ መመከት እና ወራሪ ኀይሉ ወረራ ካካሄደባቸው የአማራና አፋር ክልሎች ሳይወጣ ባለበት መቅበር የመላ ኢትዮጵያውያን አሁናዊ ተጋድሎ ነው፡፡ በዚህም ሁሉም ኢትዮጵያውያን ከፀጥታ ኀይሉ ጋር በመቀናጀት በአኩሪ ድል በሁሉም ግንባሮች ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኀይልን እየቀበሩት ይገኛል፡፡
ይህንን ወቅታዊ አጀንዳ አስመልክቶ በምዕራብ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በተካሄደ ሕዝባዊ ውይይት ሕዝቡ ለሰራዊቱ አስተማማኝ ደጀን ከመሆን ጀምሮ ግንባር እስከ መዝመት የደረሰ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑ ተነስቷል፡፡

የተጀመረው የህልውና ዘመቻ በድል እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን የተናገሩት አቶ በላይነህ ሀገር ሉዓላዊነቷ ተጠብቆ እንዲቀጥል ሁሉም በጋራ ሊነሳ ይገባል ብለዋል፡፡


የኢፌዴሪ ሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም “በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኀይል የተከፈተብንን ጦርነት በድል ለማጠናቀቅ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ውስጣዊ አንድነታችን ልናጠናክር ይገባል” ብለዋል፡፡ የተጀመረውን የህልውና ዘመቻ በድል ለማጠናቀቅ አንድነት፣ አስተማማኝ ደጀንነት እና ሠራዊቱን መቀላቀል የሚሉ ወሳኝ ተግባራትን ማከናወን እንደሚጠበቅም አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዘመኑ ይርጋ – ከፍኖተ ሰላም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation