
በአማራና አፋር ክልሎች ለተፈናቀሉ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ መንግሥት አስታወቀ፡፡
ሕዳር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ክልል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች የሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ወገኖች ባለፉት ሦስት ቀናት ብቻ 265 ሺህ 291 ኩንታል የምግብ እህል እንዲደርስ ተደርጓል፤ በዚህም ከአንድ ሚሊየን በላይ ወገኖችን መደገፍ ተችሏል ብለዋል፡፡
በአፋር ክልል በጦርነት ምክንያት ባለፈው አንድ ወር ውስጥ 76 ሺህ አካባቢ የሚደርሱ ዜጎች ተፈናቅለዋል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታዋ ለእነዚህም ወገኖች ከ36 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፎቹ በመንግሥትና በአጋር አካላት ትብብር የተደረጉ እንደሆነም ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ:- ደጀን አምባቸው
