በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው ብርሃን የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ተመረቀ::

296

ባሕር ዳር፡ መስከረም 22/2012 ዓ/ም (አብመድ) በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት የተገነባው ብርሃን የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ግንባታ ተጠናቅቆ ዛሬ ተመርቋል፡፡ ታኅሳስ 28 ቀን 2011ዓ.ም የዘውዲቱ መሸሻ የሕጻናት ማሳደጊያን የጎበኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የቃጠሎ አደጋ የደረሰበትን የሕጻናት ማሳደጊያ ለመደገፍ ቃል በገቡት መሠረት የካቲት 2011ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦለት በ12 ሚሊዮን ብር ወጪ ሲገነባ ቆይቷል::

ማዕከሉ 72 ሰዎችን የሚያስተናግድ ቤተ መጻሕፍት፣ መመገቢያ አዳራሽ፣ ምግብ ማብሰያ፣ የአስተዳደር ቢሮ፣ 96 ሕጻናትን የሚያሳድሩ መኝታ ክፍሎችን እንዲኖሩት ሆኖ ነው የተገነባው::

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በምረቃው ላይ ባደረጉት ንግግር ተባባሪ አካላትን በማመሥገን ቀጣይ ሥራዎችን አብሮ ለመሥራት የጽሕፈት ቤታቸው በር ክፍት መሆኑን አስታውቀዋል::

ምንጭ፡- የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት

Previous article“ዋጋ ያስከፈለን ግቡ የማይሳካ የፖለቲካ ልምሻ ነው፡፡” አሰተያዬት ሰጪዎች
Next articleበጥናት ላይ የተመሰረተ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድና ለችግሮች መፍትሄ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ሰላምና ደኅንነት ግንባታ ቢሮ አስታወቀ፡፡