
ሕዳር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች “ተከትለንሃል” በሚል ሐሳብ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዐቢይ አህመድ (ዶ.ር) ን በመከተል ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የከተማዋ ነዋሪዎች የሀገር ሉዓላዊነትን ለማስከበር ወደ ጦር ግንባር ለሚዘምቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች አሸኛኘት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በአሸኛኘት መርኃ ግብሩ ላይ የከተማዋ አስተዳደር አመራሮች፣ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች የአሸኛኘት ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።

