በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ከዳያስፖራው ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል።

95
ድጋፉ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የተሰባሰበ ነው ተብሏል።
ሕዳር 18/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዳያስፖራው በ’eyezonethiopia.com‘ መተግበሪያ አማካኝነት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበው ገንዘብ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊዮን ዶላር በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ አስታውቋል።
ኤጀንሲው ከቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጂስ ጋር በመተባበር ባለማውና ባስተዋወቀው እንዲሁም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዓለም አቀፍ የክፍያ መስመሩን ባመቻቸው መተግበሪያ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማሰባሰብ ተችሏል። ይህም ዳያስፖራው ምቹ ሁኔታ እስከተፈጠረለት ድረስ ሀገሩን ለመርዳት ያለውን ዝግጁነትና ዕምቅ አቅሙን አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
በድጋፉ ላይ ለተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምስጋናውን ያቀረበው ኤጀንሲው ዳያስፖራው ድጋፉን አጠናክሮ በመቀጠል የሀገር አለኝታነቱን ዳግም እንዲያረጋግጥም ጥሪ ማቅረቡን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleየሰላምና ልማት ማዕከል የተሰኘው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ፈቃድ ተሰረዘ።
Next articleየኪነ ጥበብ ባለሙያዎች “ተከትለንሃል” በሚል ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።