የኩዌት ሕዝብና መንግሥት ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

126
ሕዳር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኩዌት ሕዝብና መንግሥት በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ተፈናቅለው በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃይ ወገኖች ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል።
የኩዌት ሕዝብና መንግሥት፤ በኩዌት ዳይሬክት ኤድ በኩል በደብረ ብርሃን ከተማ ለተጠለሉ ተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦትና የብርድ ልብስ ድጋፍ ዛሬ አድርጓል።
ኩዌት ዳይሬክት ኤድ በደብረ ብርሃን ከተማ በመገኘት ከ7 ሚሊዮን በላይ ወጭ የተደረገበትን ሩዝ፣ ዘይት እንዲሁም ብርድ ልብስ ለተፈናቃዮቹ አከፋፍሏል።
የኩዌት ዳይሬክት ኤድ ካንትሪ ዳይሬክተር ጣሃ መሐመድ፤ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍ ሲያደርጉ የመጀመሪያቸው እንዳልሆነ ጠቅሰዋል።
ከዚህ ቀደም በአፋር በጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ሰዎች፣ በኮሮናቫይረስ እና ሌሎች ምክንያቶች ችግር ላይ ለነበሩ ዜጎች ድጋፍ መደረጉን አስታውሰዋል።
”የአሁኑ ድጋፍም የትብብራችን አንዱ ማሳያ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ድጋፉን አጠናክረን እንቀጥላለን” ሲሉ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
Previous articleሰበር ዜና
Next articleየሰማይ መብረቆች፣ የምድር እሳቶች!