አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ።

332
ሕዳር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አርቲስት ታማኝ በየነ እና ፖለቲከኛ አንዳርጋቸው ፅጌ ጨምሮ ታዋቂ ግለሰቦች እና የቀድሞ ጦር ሠራዊት ከፍተኛ አመራሮች ወደ ግንባር ዘመቱ።
ፖለቲከኛ ነዓምን ዘለቀ እና ብርጋዴር ጀነራል ካሳዬ ጨመዳም ወደ ግንባር ከዘመቱት መካከል ይገኙበታል።
በኢትዮጵያ ያጋጠመውን የህልውና ዘመቻ በተለያየ መንገድ ከፊት ሆነው ሲታገሉ የነበሩ አርቲስቶች እና የቀድሞ ሠራዊት የጦር አመራሮች የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ወደ ግንባር መዝመትን ተከትሎ እነሱም እንደሚዘምቱ ከዚህ ቀደም ቃል ገብተው ነበር።
በዚህም መሠረት ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና አደጋ ለመመከት ዛሬ ወደ ግንባር መዝመታቸውን ኢብኮ ዘግቧል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለህልውና ዘመቻው የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለጸ፡፡
Next articleሰበር ዜና