
ሕዳር 17/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአዲስ አበባ አንዲት እናት መኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን ብር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ለገሱ።
በአዲስ አበባ የሚኖሩት ወይዘሮ ቦጋለች ከበደ፤ የመኖሪያ ቤታቸውን ሸጠው 2 ሚሊዮን ብር ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ አድርገዋል።
ሀገር ከሌለ ሁሉም ነገር የማይቻል በመሆኑ በቤት ለመኖር ቅድሚያ ሀገርን በክብር ማኖር ይገባል በማለት ቤታቸውን ሸጠው ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው ሠራዊት መለገሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የሀገር ህልውናን ለማስጠበቅ እየተደረገ ባለው ዘመቻ ሕዝቡ ከጫፍ ጫፍ በመንቀሳቀስ በመዝመትም፤ በመደገፍም የጎላ እስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
