በኒውዝላንድ ዊሊንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቀሉ ወገኖች ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አደረጉ፡፡

82
ሕዳር 16/2014 ዓ.ም በኒውዝላንድ ዊሊንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሻባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ 30 ሺህ 995 የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ አስታውቋል፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት በኒውዝላንድ ዊሊንግተን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላደረጉት ድጋፍ ምሥጋና አቅርቧል፡፡
ኢትዮጵውያኑ እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የክልሉ መንግሥት ጥሪ ማቅረቡን ከክልሉ ገንዘብ ቢሮ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article“በጠላት መትረየስና ዲሽቃ የታሰረን ምሽግ እንደ ቀትር እባብ ተሽሎክሉኬ የቦምብ ናዳ አወረድኩባቸው፣ በየምሽጉ የነበሩት የጠላት ተዋጊዎችም የነበራቸው እድል የአሞራ ሲሳይ መኾን ብቻ ነበር” ምክትል ሳጅን አየለ ግርማ
Next articleʺበጽናት አብር በብልሃት ተሻገር”