ለወንጀል ድርጊቶች ማስፈፀሚያ ሊውሉ የነበሩ የጦር መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

169
አዲስ አበባ፡ ሕዳር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ ላይ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
በመግለጫው የአዲስ አበባ ሰላምን አስተማማኝ ለማድረግ የፀጥታ አካላት ከከተማዋ ሕዝብ ጋር በመቀናጀት ለወንጀል ድርጊቶች ማስፈፀሚያ የሚውሉ ክላሽ፣ ቦንቦች እና ተቀጣጣይ መሳሪያዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኀላፊ ቀንዓ ያደታ (ዶክተር) ገልጸዋል፡፡
የአሸባሪዎቹ የትግራይ ወራሪ ኃይል እና ኦነግ ሸኔ መታወቂያ የያዙ ግለሰቦች፣ ለአሸባሪው ኀይል ዓላማ ማስፈጸሚያ የሚውሉ የውጭ ሀገር ገንዘቦች፣ የመከላከያ እና የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ልዩ ኀይል አልባሳቶች መያዛቸውን በመግለጫቸው አብራርተዋል፡፡
ዶክተር ቀንዓ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሕገ ወጥ የደንብ ልብሶቹን ሊጠቀምባቸው ያሰበው በሐሰት መረጃ ከተማዋን ወረርኩ ብሎ ለማደናገር እንደነበር ነው የገለጹት፡፡
የጦር መሳሪያ ምዝገባዎቹ ላይ ያልተሳተፉ ግለሰቦች በአዋጁ መሰረት በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት በኀላፊነት በእጃቸው ያሉ መሳሪያዎችን በማሳወቅ ሕጉን እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡
በሕግ የተመዘገቡ መሳሪያዎችንም አካባቢያቸውን ለመጠበቅ እንዲጠቀሙበት ዶክተር ቀንዓ አስገንዝበዋል።
ጊዜያዊ መታወቂያዎች የሚሰጡት ሰላማዊ የሆኑ ዜጎችን ከአሸባሪዎቹ ለመለየት በመኾኑ ያለመንግሥት ፈቃድ መታወቂያ የሚሰጡ የግልም ኾነ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል፡፡
የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሽብርተኞችን በማጋለጥ እያደረጉት ያለው ትብብር የሚመሰገን እንደኾነ የተናገሩት ዶክተር ቀንዓ በቀጣይም ከጸጥታ አካላት ጎን በመኾን ሁሉም አካባቢውን እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ራሄል ደምሰው -ከአዲስ አበባ
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleየውጭ ሀገራት ዜጎች ከኢትዮጵያውያን ጎን በመሆን በኢትዮጵያ ላይ እየተደረገ ያለውን ተገቢ ያልሆነ ጫና እያወገዙ ነው።
Next article“የአንድ ሉዓላዊ ሀገር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ብሎ የፈረጀውን ቡድን መደገፍ የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መዳፈር ነው” የሕግ መምሕር