
ሕዳር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) እኔ እያለሁ ሀገሬ አትደፈርም፤ ከኔ በፊት ሀገሬን ያሉት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህር ረዳት ፕሮፌሰር አክሊሉ አይዛ በጥር ወር የነበራቸውን ሰርግ ሰርዘው ወደ ግንባር ሊዘምቱ ነው።
ረዳት ፕሮፌሰሩ ወደ ግንባር ለመዝመት በተዘጋጁበት ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ወደ ጦር ሜዳ ሊዘምቱ ነው የሚለውን መስማታቸው ለሀገር መከፈል ያለበትን መሰዋእትነት ለመክፈል የበለጠ ያዘጋጃቸው መሆኑንም መምህሩ ገልጸዋል፡፡

አሸባሪውን የትግራይ ወራሪ ኃይል ከመንግሥት ጎን ቆሞ መፋለም እንደሚገባም መግለጻቸውን ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ