
ባሕር ዳር፡ ሕዳር 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የማኅበሩ ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ አሸባሪው እና ወራሪው የትግራይ ኀይል ኢትዮጵያን በእጅ አዙር ቅኝ ለመግዛት ከሚፈልጉ ምዕራባዊያን ጋር ተባብሮ ወረራና ጥቃት ቢፈጽምም ኢትዮጵያ በተባበረ የልጆቿ ክንድ ዛሬም እንደትናንቱ ለነጻነቷና ለሉዓላዊነቷ መከበር እንደማትበገር ነው የተናገሩት፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያዩ ግንባሮች እየተገኙ ሠራዊቱን እያበረታቱ የቆዩ ቢሆንም አዲሱ ውሳኔያቸው ኢትዮጵያዊነታቸውን በተግባር ያሳዩበት ከመሆኑም ባሻገር ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ኀይል ለመደምሰስ በግንባር እየተፋለመ ላለው ሠራዊት ለላቀ ድል እንደሚያነሳሳው ልጅ ዳንኤል ጆቴ አስረድተዋል፡፡
ከውስጥም ሆነ ከውጭ በኢትዮጵያ ላይ የተቃጣውን የጠላት ሀሳብና ተግባር ለማምከን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፊት መሰለፋቸው ትውልዱ በተለይም ወጣቱ የአያት ቅድመ አያቶቹን የአልደፈርም ባይነት ታሪክ መድገም እንደሚያስችለው የጠቆሙት ልጅ ዳንኤል ጆቴ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበርም ሀገር ለማፍረስ የተነሳውን አሸባሪ ኀይል ለማጥፋት ሀገራዊ ኀላፊነቱን ይወጣል ብለዋል፡፡
ኅብረተሰቡ ከጠላት የሀሰት ፕሮፖጋንዳ ራሱን ማራቅ አለበት ያሉት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በርካታ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በማድረስ የሽብር ተግባር እየፈጸመ ያለውን አሸባሪውና ወራውን የትግራይ ኀይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ከመሪው ጎን መሰለፍ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በሕልውና ዘመቻው እያደረጉት ያለው ተሳትፎ ትግሉ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካንም ከእጅ አዙር ቀኝ ግዛት ነፃ የማውጣት ዘመቻ መሆኑን እንደሚያሳይ ልጅ ዳንኤል ጆቴ ጠቅሰዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ባለ ዓለምየ
#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ