❝ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ግንባር በመዝመት ሀገርን ለማዳን ያሳለፉት ውሳኔ ወቅቱን የጠበቀና በኢትዮጵያ የታሪክ ድርሳን የሚመዘገብ ነው❞ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች

165
ሕዳር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የትግራይ ዴሞራሲያዊ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሔ፤ እንደ ፓርቲ ሀገርን ከሚበታትን የሕልውና አደጋ ለመታደግ በሚያስፈልገው ሁሉ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎን እንቆማለን ነው ያሉት።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን እድገት የማይሹ የአሸባሪው የህወሓት ኃይልና ሌሎች ተላላኪዎች በሀገር ላይ እያሳደሩ ያለውን ጫና በጋራ መመከት ሀገራዊ ግዴታ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም ፓርቲያቸው ሀገርን ለማዳን በሚደረገው ማንኛውም ተግባር በጋራ ለመሥራትና ለኢትዮጵያ ህልውና መጠበቅ እስከ ግንባር ድረስ ለመዝመት ቁርጠኛ አቋም ማስቀመጡን በመግለጽ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግንባር በመሰለፍ የህልውና ዘመቻውን ለመምራት መወሰናቸው ለውጥ የሚያመጣ መሆኑንም ነው ያነሱት፡፡
በህልውና ዘመቻው በመሳተፍ ኢትዮጵያን ለማዳን መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ መጋቤ ብሉይ አብርሃም ናቸው።
“ኢህአፓ ኢትዮጵያን የማዳን ጽኑ አቋም አለው” ብለዋል፡፡
ሁሉም ኢትዮጵያዊያን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፈለግ በመከተል የህልውና ዘመቻውን በድል ለማጠናቀቅ ሚናቸውን መወጣት እንደሚጠበቅባቸውም አስገንዝበዋል።
በኢትዮጵያ አሻንጉሊት መንግሥት ለመመስረት ለቋመጡ አካላት ትምህርት መስጠት እንደሚገባ አመላክተው፤ “በድል ተመልሰን ለዓለምአቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ አሸናፊ መሆኗን እናሳያለን” ነው ያሉት።
የእናት ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰይፈስላሴ አያሌው፤ ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን የሕልውና አደጋ ለመመከት በሚደረገው ጥረት ላይ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ ሂደት ቀያሪና የዓድዋ ድልን ለመድገም እድል ይሰጣል ብለው እንደሚያምኑም ጠቁመዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) “ኢትዮጵያ” የሚለውን የነጻነት ስም የማስጠበቅ የታሪክ አደራ አለብን! ሲሉ ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous articleበኩር ጋዜጣ ሕዳር 13/2014 ዓ.ም ዕትም
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በግንባር አመራር እየሰጡ እንደሚገኙ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡