“የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጥሪና ውሳኔ ታሪካዊና ወቅቱን የጠበቀ ነው” ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ

177
ሕዳር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለኢትዮጵያውያንና ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ያስተላለፉት ጥሪና የወሰኑት ውሳኔ ታሪካዊና ወቅቱን የጠበቀ ነው ሲሉ አንጋፋው የታሪክ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ገለጹ።
ፕሮፌሰር ላጲሶ ጌዴሌቦ ለኢፕድ እንደተናገሩት፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አርዓያ ለመሆንና በተግባርም የኢትዮጵያን ጠላት ለመዋጋት መወሰናቸው እንደ ታሪክ ሊቀመጥ የሚችል ነው።
ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከዓድዋ ጋር በተመሣሣይ ደረጃ ሊገለፅ በሚችል ዓይነት ጦርነት ውስጥ ያለችና ይሄንንም ከውጭ የጥቁር ዜጎች ጠላት ከሆኑት አንዳንድ ምዕራባውያን፤ በውስጥ ደግሞ ባንዳና የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት ከሆነው ከአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል ጋር የገባነውን የሕልውና ዘመቻ አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜውን የዋጀ ንግግር አድርገዋል ነው ያሉት።
“ከፊታችን የተደቀነውን የሕልውና ስጋት አሸንፎ ሀገሪቱን ከማስቀጠል አንፃር መሪዎች እንደዚህ አይነት ንግግር ማድረግና ሕዝባቸውን የበለጠ ማነሳሳት
አለባቸው” የሚሉት ፕሮፌሰር ላጲሶ፤ በዓድዋ ጊዜም ዳግማዊ ምኒልክ ሕዝቡን ለማነሳሳትና ከኋላቸው ደጀን ሆኖ እንዲከተላቸው ይሄንኑ ነበር የተጠቀሙት ሲሉ ሐሳባቸውን ገልጸዋል።
እንደ ፕሮፌሰር ላጲሶ ገለጻ፤ የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል የአንዳንድ ምዕራባውያንን የውክልና ጦርነት ወስዶ እየተዋጋ ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ እንደለመደችው የጥቁር ሕዝቦችን ነፃነት ለማስመለስ ውክልና ወስዳ እየተዋጋች ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ ሁሉም የጥቁር ሕዝብ ከኢትዮጵያ ጎን ይቁም ያሉትም ጦርነቱ የኢትዮጵያ ብቻ እንዳልሆነ የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ ዓድዋ ላይ ባስመዘገበችው ድል በመላው ዓለም የሚገኙ የጥቁር ሕዝቦች እንደሚኮሩ ሁሉ አንዳንድ ምዕራባውያን የውስጥ ጠላቶችን ተጠቅመው የኢትዮጵያን አንገት በሚያስደፋ ተግባር ሲሳተፉ ደግሞ ከፊት ሆነው ሊሟገቱላትና ክብሯን ለማስጠበቅ ሊሰሩላት ይገባል ነው ያሉት።
በአሁኑ ጊዜ ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር የጠቅላይ ሚኒስትሩን ፈለግ መከተል እንደሚገባና ወጣቱም ሆነ የተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ መሪውን በመከተል የሀገሩን ሕልውና ማስጠበቅ እንደሚገባም ፕሮፌሰር ላጲሶ ጥሪ አስተላልፈዋል።
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
Previous article❝እኛ መስዋእት ሆነን የኢትዮጵያን ሕዝብ አንገት ቀና ካላደረግን መጪው ትውልድ አንገቱ እንደተሰበረ ይቀራል❞ የኢንደስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል
Next articleቺርቤዋ ዳር 15 ጌርክ 2014 ም.አ እትሜት